"የደጋ ሰው" ድንቅ አልበም ድምፃዊት የማርያም ቸርነት

 

ኪን/ዜና



ወጣቷ ድምፃዊት የማርያም ቸርነት (የማ) አዲስ አልበም ለአድማጮች አድርሳለች ፡፡


አልበሙ "የደጋ ሰው" ይሰኛል ።


"የደጋ ሰው" የሚል መጠርያ ያለው ይኸው አልበም 12 ሙዚቃዎችን በውስጡ ይዟል።


አልበሙ- ምርምር፣ ባህልን እና ጥበብን አካቷል ተብሏል።


የሙዚቃ አልበሙ በአይነቱ ለየት ያለ ቅርፅ ይዞ እንደመጣ የሙዚቃ ባለሞያዎች እየመሰከሩለት ነው፡፡ 


አልበሙ  ከ7 ሀገራት በላይ የሙዚቃ  ባለሞያዎች  የተሳተፉበት መኾኑን ተረድተናል።


ድምጻዊቷ የሙዚቃ አጨዋወትዋ የተመለከቱ ሁሉ  የእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)  ትመስላለች ሲሉ በአግራሞት ማድነቃቸው አልቀረም። 


ድምፃዊት የማርያም ቸርነት "ዶቃ" ለተሰኘው አለምአቀፍ ፊልም የማጀቢያ ሙዚቃ ሰርታለች፡፡ 


ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት በምትለቃቸው ነጠላ ዜማዎች ድምፃዊት የማርያም ቸርነት ተወዳጅነትን አትርፋለች፡፡ 


አልበሙ በእዩኤል መንግስቱ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ፕሮፌሽናል ሪከርዲንግ ስቱዲዮ ውስጥ እንደተቀዳ ከምንጮቻችን ሠምተናል።


በዚህ አልበም ላይ የተሳተፉት ባለሞያዎች በግጥም ዘርፍ ጎላ ጎህ፣ እዩኤል መንግሥቱ፣ ይልማ ገብረአብና አይናለም ሀዞ ናቸው፡፡


አድማጮች እስኪ ስሙትና የተሰማችሁ ስሜት አጋሩን።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)