የሰንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረት ህንፃ ተመርቋል

ቢዝነስ /ዜና 




 በ3500 ካሬ ላይ ያረፈው የሰንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረች አክስዮን ማህበር ህንፃ ተመረቀ።


የሰንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረት አክስዮን ማህበር ህንፃውን ለመገንባት ከ600 ሚሊየን ብር መዋእለ ንዋይ ፈሶበት የተገነባው ህንፃ ቅዳሜ እለት ጥር 04/ 2016 ዓ/ም መመረቁ ከቦታው ተገኝተን ተመልክተናል።


የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ያስገነባው ህንፃ የምርቃት ስነስርአት ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላት እንግዶችና በግሉ ዘርፍ ያሉ የምጣኔ ሐብት አከናዋኞች በተገኙበት ተመርቋል።


የሰንጋተራ ነጋዴዎች ህብረት አክሲዮን ማህበር በ1995 ዓ/ም በ71 አባላት የተመሰረተ መኾኑንና ማህበሩም አዲስ አበባ በተለምዶ ሰንጋተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ባለ 23 ወለል ግዙፍ የገበያ ማዕከል ተገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን የማህበሩ መስራች ነጋዴዎች ጠይቀን ነግረውናል።


                ሰንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረት ህንፃ 


አጠቃላይ ለህንፃው ቦታ 3 ሺ 500 ካሬ ሜትር  ነው። ህንፃው ያረፈበት መሬት ደግሞ 2 ሺ 800 ካሬ ላይ መሆኑ በምርቃት ስነስርዓቱ ታድመን ለመታዘብ ችለናል።


የሰንጋ ተራ ነጋዴዎች ህብረት ህንፃ ሁለት ቤዝመንት የፓርኪንግ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለው ተነግሯል ።


ከዚህ በተጨማሪም፣ ህንፃው አምስት ስመጥር ባንኮችን፣ የብሄራዊ ቲያትር ጽ/ቤት፣ ፐርፐዝ ብላክ የተሰኘው ኩባንያ ቢሮዎች፣ የተለያዩ የህንፃ መሳሪያ መደብሮች፣ የኤሌክትሪክ ግብአቶች መሸጫ ሱቆች ይገኘል።


 ሌላው ከሚሰጠው እየሰጠው ያለው አገልግሎት የጥርስ ህክምና፣ የእርዳታ ድርጅቶች መስርያ ቤቶች፣ የግል ሰራተኞች ጽ/ቤቶች፣ የምግብ አዳራሽ ካፌና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከወዲሁ ግልጋሎት መስጠት ጀምሯል ተብሏል።




                   

ህንፃው ለልማት በሚል ከዚህ ቀደም የነበሩ ሱቆች እንዲፈርሱ በወቅቱ በነበረው መንግሥት ውሳኔ ቢተላለፍም፣ ነጋዴዎቹ በራስ ተነሳሽነት 71 አባላት ያሉት ህብረት በመፍጠር አሁን ላይ ለምርቃት የበቃውን ህንፃ ለመገንባት ተችሏል።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)