በኢትዮጵያ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ጥቃት ጠቅላዩ ይቅርታ ጠየቁ

ዜና/ፓለቲካ 

 



          ፎቶ ;  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ


 

የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞች ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰማ


ባለፈው ወር የልማት ባንኩ ፕሬዝደንት አኪንዋሚ አዴሲና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ዐቢይ ለአፍሪቃ ልማት ባንክ ይቅርታ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ፅፏል።


የአፍሪቃ ልማት ባንክ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሠራተኞቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ዓለም አቀፍ ሠራተኞቹን ካስወጣ ከአንድ ወር በኋላ ሠራተኞቹ እንደሚመለሱ ማስታወቁ በዘገባው ተጠቅሷል ።


ባንኩ ዛሬ ባወጣው መግለጫም የተለመደው ሥራውን ለመጀመር የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የደህንነት ዋስትና መስጠታቸውን ገልጿል ።




የአፍሪቃ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አዴሲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ያካሄዱትን ውጤታማ ስብሰባ ተከትሎ ነው ተብሏል ።


በስምምነቱ መሠረት የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞች ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለኹ ማለቱን ተሰምቷል ።


መንግሥት ይፋዊ ይቅርታ በመጠየቁና ከክስተቱ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በተመለከተ መፍትሄ ለመፈለግ ቁርጠኝነት እንዳለውና ቃል መግባቱን ተከትሎ ባንኩ ሥራውን ኢትዮጵያ ውስጥ ይጀምራል ብሏል።


 በዑጋንዳ ካምፓላ የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ዛሬ የተካሄደ ነው። 


 ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጋር ተወያይተዋል ተብሏል ።


 ዐቢይ፣ ውይይቱን ተከትሎ "ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያለንን ግንኙነታችንን በይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረናል" ማለታቸውን በተዘገባው ተጠቅሷል ፡፡ 


ዐብይ፣ "ከባንኩ ጋር ያለን አጋርነት ለኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች ወሳኝ ነው" ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል ።


(ንጋት ፕሬስ )