"ፈናን ፔይ" የተሰኘ የክፍያ ስነስርዓት መተግበርያ ስራ ሊጀምር ነው

 ቢዝነስ /ዜና 


        የኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች (photo; dire tube)



ቢትኔት ቴክኖሎጂ ሶልሽንስ ኩባንያ "ፈናን ፔይ" የተሰኘ የክፍያ ስነስርዓት መተግበርያ የምስረታ ስነ-ስርዓት አካሔደ


ማህበሩ በከፍተኛ ባለሞያዎች ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ግብይት ስርዓትን ለማሳለጥ የሚረዳ መተግበርያ ወደስራ ሊያስገባ መኮኑን ተናግሯል።


ይኽን የሰማነው ጥር 4/2016 ዓ/ም በሒልተን ሆቴል በተደረገው የምስረታ ስነስርዓት ላይ ነው።


መተግበርያው በተለይም የንግድ ስርዓቱ አቀለጣጣፊዎች የተሳለጠ የክፍያ ስነስርዓት እንዲያገኙ ለማስቻል ነው ተብሏል።


       ቢንያም ለገሱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር (photo credit;  dire tube)


በተለይም የተቀለጣጠፈ የክፍያ ስነስርዓት ለመስጠት ያለመ መኾኑን ቢትኔት ቴክኖሎጂ ሶልሽንስ ኩባንያ የምስረታ ስነስርዓት ላይ ገልጿል።


መተግበርያው የንግድ አከናዋኞች የገንዘብ ገቢና ወጪን ጨምሮ የተለያዩ ቢዝነስ ስርአት  ውስጥ ላሉ ሁሉ በዚሁ በመመዝገብ የንግድ ሰራዎቻቸውን ማስተዳደር የሚችሉበትን ስርአት መዘርጋቱን ለማወቅ ችለናል።


በኩባንያው  ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ቢንያም ለገሱ በቢቲኔት ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ የበለፀገዉ ፈናን ፔይ የተሰኘዉ የዲጅታል የክፍያ ስርዓት ድርጅቶች አንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኦንላይን መተግበሪያቸው ሁሉንም የክፍያ አማራጮች እንዲኖራቸው የሚረዳ መኾኑን ነግረውናል።


እንደ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ገለፃ በአሁን ሰዓት በርካታ ድርጅቶች አብረው ከሚሰሩ የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ ኮሚሽን እንዲከፍሉ ይደረጋል ያለዉ ቢቲኔት ፈናን ፔይ ግን ድርጅቶች እስከ 0 በመቶ (ኮሚሽን እንዳይከፍሉ) የሚደረግበትን አሰራር ማስተዋወቁ ለማረጋገጥ ችለናል።


ይህ የሚወሰነው ድርጅቶች ባላቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴና ብቃት እንደሚሆንና ያንንም ማሳካት ለማይችሉ ተቋማት ሲስተሙ በራሱ በሚሰጠው አማራጮች በድርድር አሁን ላይ ገበያው ላይ ካለው አነስተኛውን የኮሚሽን ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል መባሉን ከማነጂንግ ዳይሬክተሩ ቢንያም ለገሱ አውቀናል።




ፈናን ፔይ ከገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነ ዘመናዊ የዲጅታል የክፍያ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችለውን ሒደት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ያሳወቀው ቢቲኔት ፋይናንስ ሶልሽን፣ በኢንተርኔት የሚደረጉ ክፍያዎችን የሚያሳልጥ፣ የንግዱ ማኀበረሰብ ግብይት ከባንኮች ጋር የሚያስተሳሰር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓትን እንደሚተገበር ተናግሯል 


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)