ምስል: ም/ሰብሳሲ ነጃት ግርማ
ቦርዱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው በአዋሽ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት አያያዛቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ፅፏል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው በአዋሽ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታቸውም የተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት አያያዝ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን በመረጃው ተጠቅሷል።
የአያያዛቸው ሁኔታ የምግብ፣ የመኝታና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶችም ተሟልተው የሚገኙ መሆኑን አይተናል ብለዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ነጃት ግርማ፤ በአዋሽ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተዘዋውረን ተመልክተን አነጋግረጠናል ብለዋል።
ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይትም በቆይታቸው ምንም አይነት የሰብዓዊ ጥሰት እንዳልደረሰባቸው ገልጸውልናል ማለታቸውን ምንጩ ተናግሯል።
የቦርዱ አባል ዶክተር አብርሃም በርታ፤ ከምልከታ ባለፈ ከተጠርጣሪዎች እና ከአስተዳደር ክፍሉ ሃላፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉን በተሰራጨው መረጃ መመልከት ችለናል።
በማቆያው በተጠርጣሪዎች ጥያቄ መሰረት መረጃ የሚከታተሉበት ቴሌቪዥን ተገዝቶ አገልግሎት እንዲያገኙ ስለመደረጉ አይተናል ብለዋል።
ከቤተሰቦቻቸው ጋርም በስልክ የመገናኘት እድሉ የተመቻቸላቸው መሆኑን ተገንዝበናል ነው ያሉት።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው በአዋሽ አርባ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት አያያዛቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።
የተጠርጣሪዎቹ ማቆያ የግብአት አቅርቦቱና የመኝታ ክፍሎች ንጽህናው የተጠበቀ መሆኑንና የህክምና አገለግሎትም በጥሩ ሁኔታ እያገኙ መሆኑን አይተናል ነው ያሉት።
በተጠርጣሪዎች የተነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የምርመራ ሂደቱ በሚፋጠንበት ሁኔታ ላይ ቦርዱ ከሚመለከተው አካል ጋር የሚነጋገር መሆኑን አረጋግጠዋል።
በምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ኮምቦልቻ ጮሪሳ ጊዜያዊ ማቆያ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቅርቡ የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው ህብረተሰቡን መቀላቀላቸው ይታወቃል።
የተመረቁት ተጠርጣሪዎች የሰላም አምባሳደርና የልማት ተዋናይ ለመሆን መዘጋጀታቸውንም አረጋግጠዋል።
(ንጋት ፕሬስ)
