ዓለማቀፍ ጀማሪ የስራ ፈጠራ ኃሳብ ውድድር በአዲስአበባ ሊካሔድ መኾኑ ተነገረ

ቴክኖሎጂ/ዜና



  ምስል: የሰራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል


ዓለም አቀፍ "የስታርትአፕ ሽልማት" በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል ተባለ።


ዓለም አቀፍ የስታርትአፕ ሽልማት ጉባዔ በአዲስ አበባ በሳይንስ ሙዚየም ከጥቅምት 14-16/2016 ዓ/ም ሊካሔድ መኾኑን ሰምተናል።


በጉባዔው ከ300 በላይ አህጉርና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የሚወዳደሩበት መኾኑን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ለንጋት ፕሬስ በላከው መግለጫ ገልጧል።


ጉባዔውን አስመልክተው የስራና ክህሎት ሚኒስትር  ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ነግረዋል።።



ከእነዚህ ውስጥ የተሻለ ስራ ይዘው ለቀረቡ 15 ተወዳዳሪዎች ሽልማት እንደሚበረከትም ተናግረዋል።


ጉባዔው የልምድ ልውውጥ የሚደረግበትና አለም አቀፍ ትስስር የሚፈጠርበት እንደሚሆንም ተስፋ ተጥሎበታል።


የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ ለሌላው አለም በማስተዋወቅ ወደ አህጉርና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ገበያ ለመግባት እንደሚረዳ ሙፈርያት ካሚል ገልፀዋል።


ሙፈርያት  አክለውም "ኔክስት ኢትዮጵያን ስታርትአፕ ኢኒሼቲቭ" ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።


 ለቴክኖሎጂ ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።


መድረኩ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ትብብር እንደሚዘጋጅ ገልጠዋል።


(ንጋት ፕሬስ)