ሰላም የፋሲካ የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ከሚያዝያ 5 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል ተባለ




 ሰላም የፋሲካ የንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል የፊታች ከሚያዝያ 5 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሔዳል ተብሏል።


 የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል የመሠብሠቢያ አዳራሽ በሰጠው መግለጫ አውርቷል።


 "ሠላም" የፋሲካ ንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል ላይ በአማካይ 15 ሺ የሚደርሱ ጎብኚዎች ይኖራሉ ተብሎ  እንደሚጠበቅ የተገለፀ ሲሆን ከ 500-600 የሚደርሱ አምራች ተሳታፊዎችም  እንደሚሳተፉ የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ዘውገ ጀማነህ ሲናገሩ ሰምተናል።


የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ዘውገ ጀማነህ እንዳሉት  በዚህ ለ33ኛ ጊዜ በሚዘጋጀው የፋሲካ ንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል አዲስ የስራ ፈጣዎች እና አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ልዩ ድጋፍ በማድረግ በአቅማቸው እንዲሳተፉ ለማስቻል መታቀዱን ገልጠዋል።


 በዝግጅቱ 500 ነጋዴዎችንም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል።


በአማካይ በቀን እስከ 15 ሺ የሚደርሱ ጎብኚዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።




በኤክስፖው ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ምርት እና አገልግሎቶች፣ የባንከ እና የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የሪል እስቴት አልሚዎችና የኢንሹራንስ ሽያጭ አከናዋኞች፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች እና የፈርኒቸር አምራችና አስመጪዎች እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ይሳተፋሉ።


 ይህን ምርታቸውን  ለማስተዋወቅ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በአቅማቸው ድንኳን ፣ ቡዝ ተከላና ሌሎች አገልግሎቶችን አጠቃልሎ በብር 50 ሺ ብር በአነስተኛ ዋጋ ተከራይተው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ማስተዋወቅና መሸጥ እንዲችሉ እድል መፍጠሩን የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ  ዘውገ ጀማነህ ነግረውናል።


የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ባለፉት 25 ዓመታት ከመንግስት ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ፣ ከም/ቤቶች ፣ ከማህበራት ዩኒየኖች እንዲሁም የግል ድርጅቶች ጋር በአጠቃላይ ከ 75 የሚበልጡ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት መቻሉ ተነግሯል።

(አማኑኤል ክንደያ)