8ተኛው ኢትዮ-ኸልዝ አውደርእይና ጉባኤ በአዲስአበባ ሊካሄድ ነው

ቢዝነስ /ዜና

      photo :  በራማዳ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጥበት


 ስምንተኛው ኢትዮ-ኸልዝ  የጤና አውደርእይና ጉባዔ በአዲስ አበባ ሚሊንየም አዳራሽ ሊካሔድ መኾኑን ተሰማ


ዝግጅቱ በአስራ ኹለት አገራት መሠረታቸው ያደረጉ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አውደርእይና ጉባኤ በሚሊንየም አዳራሽ ሊካሔድ መኾኑን ሠምተናል።


ይኽን የሰማነው የአውደርዕዮ አዘጋጆች በአዲስአበባ ከተማ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ዝግጅቱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።


ፕራና ኤቨንትስ፣ የጤና ሚኒስቴርና ሌሎች የመንግስት መስርያ ቤቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።


ኢትዮ- ሔልዝ አውደርእይና ጉባኤ ለስምንተኛ ጊዜ ከየካቲት 20 እስከ 30 2016 ዓ/ም ባሉት ኹለት ቀናት ውስጥ የሚካሔድ መኾኑን ተነግሯል ።




ይኸው ዝግጅት በአልጀርያ ንግድና ወጪ ንግድ ማስፋፍያ ሚኒስቴር ድጋፍ እንዲኹም በአልጀርያ ንግድና ንግድ ትርኢት ኩባንያ (ሳፌክስ)  አስተባባሪነት የሚዘጋጅ መኾኑን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል።


በአዲስ አበባ ሚሊንየም አዳራሽ የሚካሔደው ይኽ ዝግጅት፣ የአልጀርያ ብሔራዊ ተሳትፎን ጨምሮ ከአስራ ሁለት አገራት የተውጣጡ ከዘጠና በላይ የህክምና ንግድ አቀለጣጣፊ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት መኾኑን ተረድተናል።


አውደርእይና ጉባኤው የእውቀት ሽግግርን ጨምሮ የቴክኖሎጂ ልውውጥ እንዲኹም የንግድ ልውውጥና የገበያ ትስስርን ለማሳደግ  ያለመ ዝግጅት መኾኑን የፕራና ኤቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ ለመገናኛ ብዙሐን ሲናገሩ ተደምጠዋል።


ነብዮ ለማ አክለውም፣ "ኢትዮ-ሔልዝ ኤግዚቢሽን በጤናው ዘርፉ የተሰማሩ ንግድ አከናዋኞችን፣ የጤና ባለሞያዎችን እንዲኹም የሚመለከታቸው አጋር አካላት በአንድ ጣርያ ስር የሚመክሩበና የሚወያዮበት እድል ይፈጥርላቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል ።




በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት መኾኑንም ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ችለናል።


በዚኹ ዝግጅት ይሳተፋሉ ተብለው ከተጠቀሱ ኩባንያዎች መካከል የአልጀርያ፣ ባንግላድሽ፣ ቤላሩስ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን ፣ኢራን፣  ፓኪስታንና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ጎረቤት አገር ኬንያ የተውጣጡ መኾናቸውን በመግለጫው ተጠቅሷል።


በዝግጅቱ ከ4000  በላይ የህክምና ዕቃዎች አስመጪዎች፣ ወኪሎችና አገልግሎት ሰጪዎችን ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል ይፈጥራል መባሉን ከፕራና ኤቨርት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ ሠምተናል።


የውስጥ በኢትዮጵያደዊ ሐኪሞች ማህበርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ልብ ሐኪሞች ማህበር እንዲኹም  የተለያዩ የህክምና ማህበራት የኢትዮ -ሔልዝ  ጉባዔ  አጋሮች ናቸው ተብሏል።


ኢትዮ-ሔልዝ ጉባዔ በኢትዮጵያ ትልቁ የህክምና ሙያ ዘርፎች ተከታታይ የሞያ ማጎልበቻ መድረክ እንዲኾን ከአምናው የተሻለ ዝግጅት የተደረገበት መኾኑን ተነግሯል።


ኢትዮ-ሔልዝ ጉባዔ በአራት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግበት ነው። ማለትም በጤናው ዘርፍ አመራር ጉባዔ፣ ሜዲካል ቱሪዝም እንዲኹም ዲጂታል ሐልዝ ፎረም ይካሔዱበታል መባሉን በአዲስአበባ ራማዳ ሆቴል ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ከተሰጠው መግለጫ ማወቅ ችለናል ።



(አማኑኤል ክንደያ)



                      -Advertisement -