"ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት" የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሔዳል


         photo: ጋዜጠኛና ፕሮሞተር አብርሃም ግዛው


 ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡


አብርሃም  ግዛው  ኢንተርቴመንት  ‹‹ኢትዮጵያዊነት ዝክረ አድዋ› › የተሰኘ  የምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍና ዲስኩር የግጥም ምሽትና የስታንዳፕ  ኮሜዲ ትልቅ የኪነ-ጥበብ እና የማነቃቂያ ዝግጅቶች  እንዲሁም ስለ ሰላምና አንድነት ዙሪያ ላይ ታዋቂ ፖለቲከኞች ንግግር ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ 


በእለቱ ዶ/ር መምህር ዘበነ ለማ፣ መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣ አባሣደር ዲና ሙፍቲ፣ደራሲ ገጣሚ ፀሀፊ ተውኔትና ባለ ቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ ፣ዶ/ር ወዳጄነህ  ማህረነ፣ ዶ/ር ዮናስ ዘውዴ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ፣ሶፊያ ሸበባዉ  በእለቱ ከጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ጀግኖች አርበኞች ሽለላን ፉከራ በሻሎም የባህል ባንድ ታጅበዉ እንደሚያቀርቡ አዘጋጁ ጋዜጠኛና ፕሮሞተር አብርሃም ግዛው ለንጋት ፕሬስ ነግሯል። 




አዘጋጁ ጋዜጠኛና ፕሮሞተር አብርሃም ግዛው ተጋባዥ ሰርፕራይዝ  እንግዶች በእለቱ በመገኘት መልክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ ብሏል።


በተጨማሪም፣ የኢትዮጵያውያን የአፍሪካም ብሎም የጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ምልክት በሆነው የአድዋ ድል ዋዜማ በሚካሄው ፕሮግራም ላይ ከፍተኛ የመንግስትየስራ ኃላፊዎች፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣አርቲስቶች፣ጋዜጠኞች እና የስነ-ጽሁፍ አፍቃሪዎችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ይገኙበታል ሲል ነግሮናል።


ዝግጅቱ ሐሙስ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይከናወናል ።


በዚሁ ዝግጅት ለአገራቸውና ታሪካቸው ማወቅ፣ መረዳት፣ ማስታወስ የሚሹ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ተገኝተው እንዲታደሙ የአብርሃም ግዛው ኢንተርቴመንት መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛና ፕሮሞተር አብርሃም ግዛው ጥሪውን አቅርቧል ።


መግብያው አምስት መቶ ብር ብቻ ነው ተብሏል።


(አማኑኤል ክንደያ)




                      -Advertisement-