የቢላል የክብር እውቅና የሽልማት ሥነ ሥርዓት በሸራተን



 ቢላሉል ሐበሺ የልማትና መረዳጃ እድር ያዘጋጀው የመጀመሪያው ክብር ለባለውለታ የሽልማት ሥነሥርዓት የካቲት 18/2016 ዓ.ል ሻዕባን 16/1445ዓ.ሒ ተከናውኗል።


የቢላሉል ሃበሺ ልማትና መረዳጃ እድር «ቢላል የክብር እውቅና »በሚል ርእስ  ለሃገር ባለ ውለታ የሆኑ ግለሰቦችን ለመሸለም  እውቅና ለመስጠት እና ትውፊታቸውን ለማስቀጠል ያለመ የሽልማት ፕሮግራም በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ ዑለማዎች የመንግስት አመራሮች ፣ምሁራን ፣ባለሃብቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች እና የተሸላሚ ባለውለታዎች ቤተሰቦች በተገኙበት አከናውኗል ።


ቢላሉል ሀበሺ  የልማትና መረዳጃ ዕድር  በታላቁ ኢትዮጲያዊ ሠሀባ ቢላል ኢብኑ ረባኸ ስም «ቢላል አዋርድ»በሚል ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ  የካቲት 18/2016 ዓ.ል ሻዕባን 16/1445 ዓ.ሒ  በሸራተን አዲስ ለ5 የሀገር ባለውለታዎች እውቅና የመስጠት ሥነ-ሥርአት አካሂዶል።




በዚህ የክብር የእውቅና መርሐ ግብር :-

👉የ1966 የሚያዝያ 12 ሰላማዊ ሰልፍ አዘጋጆች

ታላቁ ዳግማዊ አባ ጅፋር ሁሴን ሱልጣን ዳውድ


👉ለ ሐጂ አቡበከር ኢብራሂም ሸሪፍ የአባድር ኢስላማዊ ትምህርት ቤት መስራች


👉ለ ፕሮፌሰር ሁሴን አህመድ የኢትዮጵያ እስልምና የምርምር ጥናት እና የታሪክ ምሁር


👉ለ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌድሌቦ የኢትዮጵያ  የታሪክ ተመራማሪና ፀሀፊ ለሆኑት የታሪክ ምሁር 


👉 የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የእኩልነት መብት እና የዜግነት ክብር እንዲረጋገጥ ለታገሉት ለሐጂ አቡበከር ሽሪፍ የእውቅናና የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።




በሕይወት ካሉት ተሸላሚዎች ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌድሌቦ ከነባለቤታቸው በቦታው ተገኝተው ሽልማታቸውን የተቀበሉ ሲሆን፣ ሌሎች ተሸላሚዎች  በተወካዮች አማካይነት ተቀብለዋል።


የ1966 የሚያዝያ 12 የሙስሊሙ መብት እንዲከበር ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ አስተባባሪ ኮሚቴ  የነበሩ አባቢያ አባ ጆቢር ዶ/ር አሕመድ ቀሎ፣  ሸህ ሰኢድ መሐመድ ሳዲቅና ሌሎችም በጋራ የተሸለሙ ሲሆን ይህንን ሽልማት ከተለያዩ ት/ቤቶች ለተውጣጡ ተተኪ ታዳጊ ተማሪዎች አበርክተዋል።


እንዲሁም በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር መሀመድ ዱሪር የሀገር ባለውለታ ለሆኑ ታላላቅ አባቶች እውቅና በመሰጠቱ የተሰማቸውን ከፍ ያለ ደስታ ገልፀዋል።


(አማኑኤል ክንደያ)