ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የአድዋ ድል በአልን አከበረ

 ዜና




ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ የአድዋ ድል በአልን አክብሯል።


ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ሰንጋ ተራ በሚገኘው የነጋዴዎች ማህበር ህንፃ በሚገኘው መስርያ ቤቱ አዳራሽ 128ኛ አድዋ ድል በአልን የተለያዩ ታሪካዊ ይዘት ባላቸው ሁነቶች ክብረ በአሉን ታሳቢ በማድረግ የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ሲያከብር መዋሉን ከቦታው ተገኝተን ተመልክተናል።


በአዳራሹ የተለያዩ አድዋ ድል በአልን የሚመለከቱ ተውኔቶች የቀረበ ሲሆን አባት አርበኞች ታድመው ክብረ በአሉን ሲያናውን እንደነበር አይተናል።


ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በአድዋ የተገኘውን ድል የአሁኑ ትውልድ ኢኮኖሚያዊ ድል በማስመዝገብ ሊደግመው ይገባል የሚል እምነት እንዳለው ሠምተናል።


ኩባንያው ውጥኑን ለማስፋፋት በተለያዮ የአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር በመስራት ላይ ነው።




ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ የጥቁሮች የኢኮኖሚ ልህቀት( Black excelency) ማምጣት ይኖርባቸዋል በሚልና የአፍሪካውያን የኢኮኖሚ ችግር መፈታት ይኖርበታል በሚል ኃሳብ የተጠነሰሰው በዩናይትድስቴትስ ነበር።


ኩባንያው ወደ አገር ቤት ሲገባ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ በብዛት እየተስተዋለ ያለውን ምግብን ዋስትና አለመረጋገጥ ለመፍታት አልሞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።


በአገር ቤት ከጀመራቸው ስመ ጥር እቅዶች መካከልም ከገበሬው የሚል እንቅስቃሴው የሚታወቅ ኩባንያ መሆኑን ይነገርለታል ።




ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በእውቁ የምጣኔ ሐብት አከናዋኝ በዶክተር ፍስኃ እሸቱ ኃሳብ አመንጪነት የተጠነሰሰ በግብርናው ዘርፍ ተሰማርቶ እንደሀገር ያሉ ምግብ ነክ ጉዳዮችን ለመፍታት የተቋቋመ ኩባንያ ነው። 


የኩባንያው መስራችና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ፍስሀ እሸቱ በአገር ቤት በርካታ የቢዝነስ አውታሮች ላይ ተሰማርተው የቆዩ የምጣኔ ሀብት አቀለጣጣፊ ናቸው።


ፍስሃ እሸቱ በተለያዮ ግፊቶች ወደ ዩናይትድስቴትስ ከማቅናታቸው በፊት ካቋቋሟቸው ኩባንያዎች መካከል ዮኒቲ ዮኒቨርስቲ እንዲሁም እለታዊ የተሰኘ ጋዜጣ መስርተው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ይታወቃል።


አሁን ላይ ከገበሬው በሚል በንግድ ሰንሰለቱ ያሉ አላስፈላጊና ለዋጋ ንረት ምንጭ የሆኑት ደላሎችን ያስቀረ ሰርአት ለመዘርጋት በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ላይ በብርቱ እየሰራ ያለ ኩባንያ በማቋቋም እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ።


ከዚህ በተጠማሪም ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በቤት ልማት ዘርፍ ተሰማርቶ እየሰራ የሚገኝ አገር በቀል ኩባንያ ነው።


ኩባንያውን ለመደገፍና በመገናኛ ብዙሐን ዘርፍ ተሰማርቶ ለመንቀሳቀስ ኬ ቲቪ የተሰኘ ቴሌቪዥን ጣብያ አቋቁሞ  በመንቀሳቀስ የሚገኝ ኩባንያ መሆኑን ሠምተናል። 


(አማኑኤል ክንደያ)


                    - Advertisement -