ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን ሲሉ ሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ቅሬታቸውን ገለፁ

 

አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅና የቀድሞው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ መካከል እየተስተዋለ ያለውን ልዩነት በተሽከርካሪ አስመጪዎች  ላይ ጫና እየፈጠረ ነው የሚል ቅሬታ እየተነሳ ነው። የጉምሩክ ኮሚሽን በዘፈቀደ ጨረታ ያወጣባቸው ተሽከርካሪ አስመጪዎች ስሞታቸውን ለንጋት ፕሬስ አቅርበዋል ። በጉዳዩ ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነውን ሰነድ ተመልክተን ፣ የአስመጪዎቹ ቅሬታ አሰባሰበን ተከታዩን ዘገባ አጠናቅረናል። የንጋት ፕሬስ አዘጋጅ አማኑኤል ክንደያ ተከታዩን አዘጋጅቷል። ዝርዝር ዘገባውን አንብቡት 




ሳኡዲ አረብያ ኑሯቸውን  ያደረጉ ወገኖች  ከሚደርስባቸው በደልና የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚደርስባቸው በደል የሚታወቅ መሆኑ እሙን  ነው።  በዚህ መሠረትም  ወደ አገራቸው እንዲመለሱና ንብረታቸውን በተለይም የግል የስራ ተሽከርካሪ መኪኖችን ወደ አገር ቤት ማስገባት እንደሚፈልጉ በደብዳቤ ለመንግሥት እየገለፁ መቆየታቸውን የሚታወቅ ሆኖ ሳለ በጊዜ ሂደት ጉዳዩን በመንግሥት ይሁንታ ማግኘቱን  ይታወቃል ።


ስለዚህም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ በተደነገገው መሠረት አሮጌ ተሽከርካሪዎች በነባሩ ማስከፈያ ምጣኔ ኤክሳይዝ ታክስ የተከፈለባቸው ጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኃላ ቁጥራቸው ወደ 297 የሚሆኑ ያገለገሉ  ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ መንግሥት ፍቃድ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።


ይሁንና  የገንዘብ  ሚኒስትር ያሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ ወደ ጎን በማለትና የህግ አግባብ ባልተከተለ መልኩ መኪኖቻችንን በሐራጅ እንዲሸጡ እንቅስቃሴዎች የተጀመረ ሲኾን፣ ይህንኑ ትልቁ መንግስታዊው አካል የገንዘብ ሚኒስቴር ያሳለፈው ውሳኔ ሳይከበር ቀርቶ በሰው አገር ጥረን ግረን ያፈራነውን ንብረት በማን አለብኝነት የጉምሩክ ኮሚሽን በሐራጅ ለመሸጥ እየተሰናዳ ይገኛል ብለዋል።


አህመድ ሺዴ ገንዘብ ሚኒስትር 


ከአረብ አገር ስደት ተመላሾች እንደሚሉት" እኛ እንደ ዜጋ ለከፍተኛ ኪሳራ በመዳረጋችን ሳቢያም  የሚመለከተው የመንግስት አካል ተሽከርካሪዎቻችን በሐራጅ ለመሸጥ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እንዲያስቆምልን እንጠይቃለን" ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ባሰራጩት  ደብዳቤ ለመረዳት ችለናል ።


በአጠቃላይ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ፍቃድ ከተሰጣቸው ተሽከርካሪዎች ወደ " 297 " ገደማ ሲኾኑ  "37 " ያህል ተሽከርካሪዎች በጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ  ለመንግሥት መሰርያ ቤት አገልግሎት እንዲውሉ መደረጋቸውን ጠቅሰው፣ ሌሎች  "23 " ተሽከርካሪዎች ደግሞ በሽያጭ እንዲወገዱ ተደርገውብናል ብለዋል። አሁን ላይ ደግሞ  የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት "237" ተሽከርካሪዎች በሐራጅ ሽያጭ እንዲወገዱ በሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው አስፈላጊውን የመንግሥት አካል ያለንበትን ችግር በመረዳት መፍትሔ እንዲሰጠን  ሲሉ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ ።


እነዚህ በሐራጅ እንዲሸጡ የጉምሩክ ኮሚሽን የሐራጅ ማስታወቅያ ካወጣባቸው ዜጎች በአገር ውስጥ ተሽከርካሪዎች በማስመጣት ስራ ላይ የተሰማሩ አስመጪዎች የሚገኙበት ሲሆን ከአረብ አገር ተሽከርካሪዎቻቸው ይዘው እንዲገቡ በመንግሥት ፍቃድ ከተሰጣቸው ዜጎች በተጨማሪ  10 የአገር ውስጥ ተሽከርካሪ አስመጪዎች ይገኙበታል ።


 እነዚህ  297 ተሽከርካሪዎች አዲሱ የኤክስሳይዝ  አዋጅ 1186/2012  ከመፅደቁና ከመውጣቱ በፊት ተገዝተው የገቡ መኾናቸውንና በወቅቱ ወደ አገር ቤት ማስገባት ያልተቻለበትን ምክንያትም "በአለማቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ሳቢያ የወደብና ሌሎች የሎጂስቲክስ አገልግሎት ማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው" መኾኑን በመግለፅ ለገንዘብ ሚኒስቴር አህመድ ሺዴ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ገልፀው "በቀድሞ የኤክሳይዝ የታክስ ተመን" ከፍለው ተሽከርካሪዎች ማግኘት እንደሚችሉ ይሁንታ ማግኘታቸውን ይናገራሉ።




የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው ለሚመለከተው አካል ሁሉ በፃፉት ደብዳቤ መሰረት "ተሽከርካሪቹ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ የፈሰሰባቸው  በመኾናቸውና ተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶችም  ቢሆኑ  ለዘመናት ባጠራቀሙት  ጥሪት የገዟቸው ንብረቶች በመኾናቸው፣  መንግሥት (የገንዘብ ሚኒስቴር ) እነዚህ ዜጎች የገጠማቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  ችግር በመገንዘብ ቀድሞውኑ በነበረው ወይንም ከመሻሻሉ በፊት  በነበረው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ  ታክሱን ከፍለው መኪኖቹን እንዲወስዱ" የውሳኔ ሀሳብ  ማሳለፉን በአህመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣውንና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ሰነድ ለመረዳት ችለናል።


ሌላኛው አህመድ ሺዴ ለሚኒስትሮች ምክርቤት ያቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ  "በሐራጅ ከተሸጡ 23 ተሽከርካሪዎች ከተገኘው ብር 23,603,866,94 ውስጥ በቀድሞው ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅና ሌሎች ህጎች መሠረት ሊከፈል የሚገባውን ቀረጥና ታክስ ተቀንሶ ቀሪው ሒሳብ ለአስመጪዎቹ እንዲመለስላቸው" በደብዳቤው ገልፀዋል።


ለመንግስት መስርያ ቤቶች የተከፋፈሉት " 37  ተሽከርካሪዎች በሚመከት የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ተቀንሶ ብር 21,902,845,88  ለአስመጪዎቹ እንዲመለስላቸው" ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ በደብዳቤያቸው አስረድተዋል ።




የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ለህዝብ እንደራሴዎች  ለምክርቤት ግልፅ ደብዳቤ ቢፅፉም  ውሳኔ ቢያሳልፉም እየተከበረ ባለመኾኑ የጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር  ምክረሀሳብ የሚፃረርና የተሳሳተ መንገድ እየሔድ መኾኑን ከሰደት ተመላሽ  ዜጎችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ይናገራሉ። 


የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ " በቀድሞውና በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ያለው ልዩነት የሚከፈለው ታክስ በምህረት ቀሪ እንዲደረግ"  ለህዝብ ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት   የውሳኔ ሀሳብ ማቅረባቸውን በሰነዱ ላይ ተመላክቷል። 


በዚሁ መሰረት መኪኖቹን ለመውሰድ ያደረግነው ሙከራ የጉምሩክ ኮሚሽን ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ ከአረብ አገር ሰደት ተመላሽ ዜጎችና የአገር ውስጥ ተሽከርካሪ አስመጪዎች ለመገናኛ ብዙሃን የገጠማቸውን  ችግር ተናግረዋል ።


 እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት  "ይባስ ብሎም የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው  የሐራጅ ማስታወቅያ  የወጣባቸውን ጥረው ግረው ያፈራቸው ተሽከርካሪ ንብረቶቻችን ( መኪኖቻችን ) ሊሸጡብን በመኾኑ የገንዘብ ሚኒስቴርን ጨምሮ  የሚመለከተው የመንግሥት አካል ድርጊቱን እንዲያስቆምልን እንጠይቃለን ሲሉ ከአረብ አገር በሰደት የነበሩ ወገኖችና የአገር አስመጪዎች ውስጥ አስመጪዎች ቅሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ።


በህገመንግሥቱ በተቀመጠውና በተሰጠን መብት  መሰረት በአገራችን ንብረት የማፍራትና የንብረት ባለቤት የመኾን መብቶቻችን በማን አለብኝነት እየተጣሰ ይገኛል ሲሉ እየገለፁ ነው።


ለዚህም የሚመለከተው የመንግስት አካል ችግራችንን ተረድቶ አስፈላጊውን መፍትሔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ብለዋል።



(ንጋት ፕሬስ)