ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በጀርመን የነበራቸው ቆይታ ውጤታማ ነበር - ቢልለኔ ስዩም

 

      ቢሊሌኒ ስዮም  ፕሬስ ሴክረተሪ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጀርመን የነበራቸው ቆይታ ውጤታማ  ነበር ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም ገለፀዋል።


 ዐቢይ በጀርመን በተካሄደው "ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ" ጉባዔ  ላይ መሳተፉ ይታወቃል፡፡


በዚህ ወቅት የኢትዮጵያና ጀርመን መሪዎች የተወያዩባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ቢልለኔ በሰጡት ማብራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ጋር የሁለትዮሽ የተሳካ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል ፡፡


ውይይቱ ከዚህ በፊት መክረውባቸው የነበሩትን የሁለትዮሽ ጉዳዮች የበለጠ ማጠናከር፣ ቀጣናዊ ጉዳዮችንም የበለጠ ተሳስሮ መስራት ላይ ያተኮረ እነደሆነ ቢልሊኔ ስዩም አስታውቀዋል፡፡


ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች እገዛ የምታደርግ ሀገር መሆኗን የገለጹት ሃላፊዋ ፥ በታዳሽ ኃይል፣ በትምህርት፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የበለጠ አብሮ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ" ጉባዔ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለውን ተግባራት፣ የተፈጠሩ ክፍተቶችን እና ማሻሻያዎችን አስመልክተው ሃሳባቸውን ማካፈላቸውን ቢልለኔ  ተናግረዋል፡፡


 ዐቢይ   ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዔል ማክሮን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውንም በማብራርያቸው ጠቅሰዋል ፡፡


በቆይታቸው ከዚህ በፊት መክረውባቸው የነበሩትን ጉዳዮች ለማደስና የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረኮችም ያላቸውን ሚና ለመጫወት ተወያይተዋል ነው ያሉት፡፡


በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀርመን ቆይታ ስኬታማ እንደነበርም  ነው ቢልለኔ ስዩም ሲናገሩ ተደምጠዋል ፡፡


(ለንጋት ፕሬስ ንጉሴ መንገሻ)