ሽታዮ ስዊት ሆቴል የፊታችን የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስአበባ ሊመረቅ ነው

ቢዝነስ /ዜና


        photo : ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ [ፎቶ መጎስ መኮንን]


 ሽታዮ ስዊት ሆቴል ዘመናዊ የኾነ ሆቴል በአዲስአበባ ከተማ ወሎ ሰፈር ጎርጎርዮስ አደባባይ ፊትለፊት አለማቀፍ ሆቴል አስገንብቶ በይፋ ስራ መጀመሩን ሰምተናል።


የሽታዮ ስዊት ሆቴል ባለ ቤት አቶ ሸዋረጋ ቢረዳ ይባላሉ።


አቶ ሽታዮ ቢረዳ ከ36 አመታት በፊት በሐምሳ ብር መነሻ ሒሳብ ወደ ምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ መግባታቸውን ከባለሀብቱ ድህረ ታሪክ መረዳት ችለናል።



ሽታዮ ሰዊት ሆቴል የተለያዩ ላውንጅ፣ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች ያሉት ሲኾን የተቀናጡ ከቱርክ አገር በገቡ እቃዎች የተሰራ ነው ተብሏል።




 በአገር ቤት የከፈተው ይህን ሆቴል  በአለማቀፍ ደረጃ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በመባል የሚታወቀው የሆቴል ስራ በመጀመር የመንግሥት የአምስት አመቱ የአገር በቀል ኢኮኖሚ እድገት እቅድ አካል ለመኾን ውጥን ይዞ ወደ ሆቴል ዘርፍ መሰማራቱ ተናግሯል ።


ይኽን የሰማነው ሽታዮ ስዊት ሆቴል ለአገርውስጥ መገናኛ ብዙሐን ባለሞያዎች የሆቴሉን አጠቃላይ የደረሰበትን ደረጃ ባስጎበኘበት እለት ነው።


 ሽታዮ ስዊት ሆቴል የኩራዝ ወንዝ ኃ/የተ/የግ/ ድርጅት አጠቃላይ ፕሮጀክት አንደኛ እህት ኩባንያ ነው።


ሽታዮ ሰዊት ሆቴል ከፍተኛ የኾነ መዋእለ ንዋይ የፈሰሰበትና በሆቴል ዘርፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ ውጥን ይዞ እንቅስቃሴ የጀመረ መኾኑን የሆቴሉ  ዋና ስራ አስኪያጅ አዳም በቀለ  ተናግረዋል ።


ሽታዮ ስዊት ሆቴል በ600 ካሬ ላይ ያረፈ G+15 ከአንድ ቤዝመንት ጋር አጣምሮ የያዘ ሆቴል  ነው ተብሏል።


         photo:  ሸዋረጋ ቢረዳ የሆቴሉ ባለቤት [ፎቶ ሞገስ መኮንን]


ሆቴሉ ግንባታ ከቱርክ አገር የመጡ የሆቴልና ኮንስትራክሽን ጥሬ የመጡ እቃዎች የተገነባ ሆቴል መኾኑን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳም በቀለ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ ሰምተናል።


   

ሆቴሉ የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር ከሁለት መቶ  በላይ ስራተኞች የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል።


65 የራሳቸው ማብሰያ የተገጠመላቸው ክፍሎች ያሉት ሲኾን ክፍሎቹ ባለ አራት መኝታ ቤቶች መኾናቸውን ተመልክተናል ።


ክፍሎች በዘርፉ ቋንቋ "ኮኔክትድ ሩምስ" ይሰኛሉ።


በቂ የመኪና ሚቆምያ እንዳለውና አለማቀፍ እንግዶች ፣ የመንግሰት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ማስተናገድ የሚችል መኾኑን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳሙ በቀለ ሲናገሩ ሰምተናል።


በቅርቡ የሽታዮ ስዊት ሆቴል እህት ኩባንያ የሆነው ኩራ ሪልስቴትና ሬዲሚክስ ኮንክሪት (ready mix concrete batching plant ) እንደሚጀምሩ 

ለማወቅ ችለናል።


የሆቴል ኢንዱስትሪ የኮቪድ 19 ተህዋሲ መከሰት ወዲህ ገበያው እጅግ ተቀዛቅዞ እንደነበር ይታወሳል።  


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



                         -Advertisements-