ከለሊቱ 6:00 ሰአት የተሰኘ ፊልም ሰኞ 'ለት ሊመረቅ ነው ተባለ

ኪን/ዜና 





 ከለሊቱ 6:00 የተሰኘውን ፊልም ሰኞ 'ለት ሊመረቅ ነው


ከ3 ሚሊዮን ብር ወጪ የወጣበት “6፡00 ሰዓት ከሌሊቱ” ፊልም በብሔራዊ ቲያትር ይመረቃል መባሉን ከአዘጋጆቹ ተረድተናል።



ከለሊቱ 6:00 የተሰኘውን ፊልም ላንጋኖ፣ ሻኪሾ፣ አዋሳ ፣ ሞጆ፣ አዶላ ቀረፃ ተደርጎለታል ተብሏል ።


ከለሊቱ 6:00 ሰአት በኤልዳን ፊልም ኘሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በ' በሽ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በመርገድ ፊልም ኘሮዳክሽን ጋር  በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑን ሲነገር ሰምተናል።




 "6፡00 ሰዓት ከሌሊቱ" ፊልም  የፊታችን ሰኞ'ለት መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቲያትር ይመረቃል ተብሏል።


ፊልሙ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራች፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በይፋ እንደሚመረቅ ሰምተናል።


የፊልም ምርቃት መርሐግብር አስመልክቶ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር በሃይሉ እንግዳ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም በቤስት ዌስተርን ፕሪሚዬም ሆቴል ለመገናኛ ቡዙሃን ባለሙያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


ፊልሙን ከሶስት አመት በላይ  እንደፈጀ በመግለጫው ተጠቅሷል።





ፊልሙ አርቲስት ሠላም ተስፋዬ ፣ አርቲስት ማርታ ጎይቶም ፣ አርቲስት ነብዩ እንድሪስ ፣ አርቲስት ሠይፈሚካኤል ተስፋዬ ፣ አርቲስት ሚኪ ተስፋዬ ጨምሮ ሌሎች ተዋንያን እንደተሳተፉበት ገልጸዋል።


ከሰባት በላይ ቦታዎችን መቼቱ ያደረገው  “6፡00 ሰዓት ከሌሊቱ” ፊልም ከመጋቢት 6 ቀን  2016ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች ለዕይታ ይበቃል።


(አማኑኤል ክንደያ )