የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ያዘጋጀው የጤና አውደ ርዕይ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ

ጤና/ዜና




 የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ያዘጋጀው የጤና አውደ ርዕይ  በአዲስ አበባ ተከፈተ


አውደርዕዩ በአዲስአበባ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፍቶ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል።


ማህበሩ 60ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽን በማከናወን እያሳለፈ ይገኛል።



ዕድሜ ጠገቡ የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የተመሰረተው 1954 ዓ.ም ነበር።




ማህበሩ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ፤ በታካሚዎች ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫጠት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ማህበር ሐኾኑ ይታወቃል።


የማህበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለፀን ማህበረሰብ ማየት መሆኑን በመክፈቻ ስነስርዓት ሲነገር ሰምተናል።


ይህንን እውን ለማድረግ በብርቱ እየሰራ መሆኑን የሚታወቅ የህክምና ህብረት ነው።




 ማህበሩ ከሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተለይም የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም ከስፒሻሊቲ ሶሳይቲዎች እና ከማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት 60ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽን ከዛሬ  የካቲት 29 - 30 ማካሄድ ጀምሯል።


(አማኑኤል ክንደያ)