ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ በርትቼ እየሰራሁ ነው አለ



ቢዝነስ/ዜና


       photo: ብርሐን ተድላ የኢትዮ- ኢስታንቡል ሆስፒታል ባለቤት


 ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ለህክምና ወደ ውጪ ሀገር የሚደረጉ ጉዞዎችን ለማስቀረት እየሰራሁ ነው አለ።


ሆስፒታሉ 106 እውቅ የህክምና ዶክተሮች አማካኝነት የህክምና ስራውን እያቀለጣጠፈ መኾኑን ተረድተናል።


ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ወደ ስራ ከባሁ ምንም እንዃን አጭር ጊዜ ቢሆንም ስራዮን በወጠንኩት ልክ እየሄደልኝ ነው ማለቱን በስካይ ላይት የነበረው ዝግጅት ላይ ሰምተናል ።


የሆስፒታሉ ባለቤት አቶ ብርሀን ተድላ ድርጅታቸው ላለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸው ስራዎችን አስመልክተው ለሰራተኞቻቸው የምስጋና መርሐ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል አከናውነዋል።


ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በ2020 ዓ.ም ዓለም-አቀፍ መመዘኛዎችን ያሟላ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር-ቀደም የሆነ ሁሉን አቀፍ የህክምና ማዕከል ነው። 




 ከተመሰረተ 6 ወራት ሆኖታል።


በዚህ የስድስት ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ክንውን የሆስፒታሉ ሰራተኞች፣ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የካቲት 30/2016 ዓም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነበር።። 


በፕሮግራሙ ላይም፣ የመጀመሪያውን ቀዶ ሕክምና ጁላይ 18 ቀን 2023 በተሳካ ሁኔታ በማከናወን የቀዶ ህክምና ስራ የጀመረው ኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል በ17 ስፔሻሊስት እና በ89 ሳብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች በአጠቃላይ በ106 እውቅ የህክምና ዶክተሮች አማካኝነት ከ4ሺህ በላይ ተመላላሽ ታካሚዎች ህክምና መስጠቱን የሆስፒታሉ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃን ተድላ ነግረውናል።


በልዩ ሁኔታ አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ክፍሎች ውስጥ ዋነኛው የተኝቶ ማከም አገልግሎት ሲሆን በዚህ አገልግሎትም ከ1 ሺህ በላይ ታካሚዎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል።


ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ 3ሺህ የሚደርስ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) ህክምና የሰጠው ሆስፒታሉ ከተቋቋመባቸው ግንባር ቀደሙ አላማ  መሠረትም የውጭ ሀገራት ህክምናዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሀገር ውስጥ መስጠት ማስቻል ነው።




ሆስፒታሉ እስካሁን ለ56 ወንዶች እና ለ130 ሴቶች በድምሩ ለ189 ቋሚ እና ለ106 የትርፍ ሰዓት ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠር ችሏል።


በእለቱ ከፍተኛ አፈፃፀም ላሳዩ ዶክተሮች እና ሰራተኞች እውቅና ተሰጥቷል።


በቀጣይ የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ፕሮጀክት አቅደናል ከመንግስት የጠየቅነው መሬት ከተፈቀደ 150 አልጋ ያለው ሂሊኮፍተር ማሳረፍ የሚችል ህንፃ በመስራት እንዲሁም የካንሰር ሴንተር በማቋቋም የካንሰር ህክምና ለማድረግ ቴክኖሎጂውን የማምጣት እቅድ እንዳላቸው አቶ ብርሃን ተድላ ሲናገሩ ሰምተናል።


(አማኑኤል ክንደያ)



                          -Advertisement-