ሽታዮ ስዊት ሆቴል በአዲስአበባ ከተማ አስመርቋል

 

   photo: ሒሩት ካሳው ባህል፣ ኪነጥበብ ቢሮ ሓላፊ [ ፎቶ;  ሞጎስ መኮንን]



ሽታዮ ስዊት ሆቴል በአዲስአበባ ያስገነባውን ሆቴል  አስመርቋል


ሽታዮ ስዊት ሆቴል ወሎ ሰፈር ጎርግረስ አደባባይ ከአከባቢ በሚገኘው የካቲት 23 ቀን 2016 አስመርቋል።


ሽታዮ ስዊት ሆቴል በ600 ካሬ ላይ ያረፈ ሲኾን ቤዝመንትን ጨምሮ ባለ አስራ አምስት ህንፃ ነው  ተብሏል።


በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳውን፣ የፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቱን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ሓላፊዎች በተገኙበት ሆቴሉ ተመርቋል።


የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ባህል፣ ኪነጥበብ ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ሒሩት ካሳው በይፋ ሆቴሉን መርቀው ከፍተውታል ።




          

ሒሩት ካሳው ለሆቴልና ቱሪዝም እንቅስቃሴ መስፋፋት የግሉ ባለሀብቶች ያላቸውን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለከተማዋ የቱሪስት መናገሻነት የሚኖረው አዎንታዊ አስተዋፅኦ የማይተካ መኾኑን ገልፀዋል።


የሽታዮ ስዊት ሆቴል ባለ ቤት አቶ ሸዋረጋ ቢረዳ ይባላሉ።


አቶ ሽታዮ ቢረዳ ከ36 አመታት በፊት በሐምሳ ብር መነሻ ሒሳብ ወደ ምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ መግባታቸውን ከባለሀብቱ ድህረ ታሪክ መረዳት ችለናል።


ሽታዮ ሰዊት ሆቴል የተለያዩ ላውንጅ፣ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች ያሉት ሲኾን የተቀናጡ ከቱርክ አገር በገቡ እቃዎች የተሰራ ነው ተብሏል።


ሽታዮ ስዊት ሆቴል ዘመናዊ የኾነ ሆቴል በአዲስአበባ ከተማ ወሎ ሰፈር ጎርጎርዮስ አደባባይ ፊትለፊት አለማቀፍ ሆቴል አስገንብቶ በይፋ ስራ መጀመሩን ሰምተናል።



   photo: አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ ሓላፊዎች ሆቴሉን ሲያስመርቁ [ ፎቶ: መጎስ መኮንን]


ሽታዮ ሰዊት ሆቴል የተለያዩ ላውንጅ፣ ካፌዎች፣ ባርና ሬስቶራንቶች ያሉት ሲኾን የተቀናጡ ከቱርክ አገር በገቡ እቃዎች የተሰራ ነው ተብሏል።


 በአገር ቤት የከፈተው ይህን ሆቴል  በአለማቀፍ ደረጃ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በመባል የሚታወቀው የሆቴል ስራ በመጀመር የመንግሥት የአምስት አመቱ የአገር በቀል ኢኮኖሚ እድገት እቅድ አካል ለመኾን ውጥን ይዞ ወደ ሆቴል ዘርፍ መሰማራቱ ተናግሯል ።


 ሽታዮ ስዊት ሆቴል የኩራዝ ወንዝ ኃ/የተ/የግ/ ድርጅት አጠቃላይ ፕሮጀክት አንደኛ እህት ኩባንያ ነው።


ሽታዮ ሰዊት ሆቴል ከፍተኛ የኾነ መዋእለ ንዋይ የፈሰሰበትና በሆቴል ዘርፍ አንድ እርምጃ ወደፊት ለማራመድ ውጥን ይዞ እንቅስቃሴ የጀመረ መኾኑን የሆቴሉ  ዋና ስራ አስኪያጅ አዳም በቀለ  ተናግረዋል ።


ሆቴሉ ግንባታ ከቱርክ አገር የመጡ የሆቴልና ኮንስትራክሽን ጥሬ የመጡ እቃዎች የተገነባ ሆቴል መኾኑን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳም በቀለ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ ሰምተናል።




ሆቴሉ የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር ከሁለት መቶ  በላይ ስራተኞች የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል።



65 የራሳቸው ማብሰያ የተገጠመላቸው ክፍሎች ያሉት ሲኾን ክፍሎቹ ባለ አራት መኝታ ቤቶች መኾናቸውን ተመልክተናል ።


ክፍሎች በዘርፉ ቋንቋ "ኮኔክትድ ሩምስ" ይሰኛሉ።


በቂ የመኪና ሚቆምያ እንዳለውና አለማቀፍ እንግዶች ፣ የመንግሰት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ማስተናገድ የሚችል መኾኑን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አዳሙ በቀለ ሲናገሩ ሰምተናል።


በቅርቡ የሽታዮ ስዊት ሆቴል እህት ኩባንያ የሆነው ኩራ ሪልስቴትና ሬዲሚክስ ኮንክሪት (ready mix concrete batching plant ) እንደሚጀምሩ ለማወቅ ችለናል።


(አማኑኤል ክንደያ)




                 - Advertisements  -