የረመዳን ፆም "ኢትዮጵያ ታፍጥር" የማዕድ ማጋራት እና የማስፈጠር መርኃ ግብር ሊከናወን ነው

            photo: ኢትዮጵያ ታፍጥር ጋዜጣዊ መግለጫ 

 "ኢትዮጵያ ታፍጥር" የማዕድ ማጋራት እና የማስፈጠር ሊከናወን ነው ተብሏል ።

የአፍጥር እና የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር  አስመልቶ በአዲስአበባ  ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መስርያ ቤት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ  ተሰጥተዋል።

 "ኢትዮጵያ ታፍጥር" የማዕድ ማጋራት እና የማስፈጠር በአራቱም ማእዘናት አዲስ አበባን ጨምሮ  ጅግጅጋ ፣አሶሳ፣ መቀለ ከተሞት ላይ ለማከናወን ውጥን መያዙን ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ነፊሳ ሲናገሩ ሰምተናል።

አጠቃላይ ከ90,000 ያህል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ወገኖች ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ድጋፉ በዋጋ ሲተመን 72 ሚልየን ብር ለማሰባሰብ ውጥን ተይዞለታል ተብሏል።

ድጋፉ ዕለታዊ እና ወርሐዊ የድጋፍ እና የምገባ ፓኬጅ በማዘጋጀት ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በመተባበር ለዕለታዊ የምግብ ፍጀታነት የሚውሉ የዘይት፣ የዱቄት፣ የሩዝ፣የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ለመለገስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረዳት ችለናል።

 የኢትዮጵያ ታፍጥር ቲም ዋና አዘጋጆች ፣ዲዛይነር ወ/ሮ ፎዚያ አወል፣  የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ዲኤታ ነፊሳ  ፣ጋዜጠኛ ሰኢድ አህመድ ፣የካሜራ ባለሙያ አብዱሌሐኪም ሐበሽ መሆናቸውን ከመግለጫው ተረድተናል ። 

ድጋፉ የሚደረገው በቀጥታ ስርጭት እና ከለጋሽ ተቋማት እና ግለሠቦች ከሚሠበሠብ ገቢ በመሆኑ  በሐገር ውስጥ እና ከሐገር ውጭ የሚገኙ ኢትጵያውያን በዚህ የበጎነት ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን ቀርቧል።

በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከጎረቤት አገራት ለሚነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ በመሥጠት እና ለአረቡ አለም አባይን እና ኢትዮጵያን በተመለከተ ተገቢ ግንዛቤ በመስጠቱ ረገድ በትጋት እየሠራ በሚገኘው ዑስታዝ ጀማል በሽር አማካይነት የሚመራው ኪንግስ ኦፍ አባይ ሚዲያ በስሩ በሚገኙት ፍሎር ዲዛይን ፣ ኢትዩጽያ ታፍጥር ቲም ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህል እና ስፖርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

 በአባይ ወንዝ ጉዳይ ላይ ከጎረቤት አገራት ለሚነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ በመሥጠት እና ለአረቡ አለም አባይን እና ኢትዮጵያን በተመለከተ ተገቢ ግንዛቤ በመስጠቱ ረገድ በትጋት እየሠራ በሚገኘው ዑስታዝ ጀማል በሽር አማካይነት የሚመራው ኪንግስ ኦፍ አባይ ሚዲያ በስሩ በሚገኙት ፍሎር ዲዛይን ፣ ኢትዩጽያ ታፍጥር ቲም ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ባህል እና ስፖርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

ድጋፉ ዕለታዊ እና ወርሐዊ የድጋፍ እና የምገባ ፓኬጅ በማዘጋጀት ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በመተባበር ለዕለታዊ የምግብ ፍጀታነት የሚውሉ የዘይት፣ የዱቄት፣ የሩዝ፣የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ለመለገስ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረዳት ችለናል።

 ድጋፉ የሚደረገው በቀጥታ ስርጭት እና ከለጋሽ ተቋማት እና ግለሠቦች ከሚሠበሠብ ገቢ በመሆኑ  በሐገር ውስጥ እና ከሐገር ውጭ የሚገኙ ኢትጵያውያን በዚህ የበጎነት ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን ቀርቧል።

ለዚህ «ኢትዮጵያ ታፍጥር» መርሐግብር  ድጋፍ የማድረጊያ የባንክ ቁጥሮች ሒጅራ ባንክ 10004019080001፣ ዘምዘም ባንክ 0031492220101 እንዲሁም በአቢሲኒያ ባንክ 178290746  ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ ተብላቹኃል።

(አማኑኤል ክንደያ)

                       Advertisement