የፌቨን ጋሻው አዲስ መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

 ኪን/ዜና


      photo:  ደራሲዋ  ፌቨን ጋሻው [ፎቶ ሲሳይ ጉዛይ]



"ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለምን ? እስከምን" የተሰኘ መፅሐፍ መጋቢት ሦስት ገበያ ላይ ይውላል ተባለ


"ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለምን? እስከምን" ከዚህ ቀደም የንጉስ ሴት ልጆች በተሰኘ መጽሐፏ የምትታወቅ ደራሲ ናት።


 የንጉሱ ሴት ልጆች በጎ አድራጎት መስራች ዳይሬክተር  ጭምርም ነች ።


 ፌቨን ጋሻው ትባላለች።




ደራሲዋ አሁን ላይ  ሁለተኛ መጽሐፏ ለማሳተም መብቃትዋ የካቲት 27/2016 ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ አስታውቃለች።


የንጉሱ ሴት ልጆች በጎ አድራጎት የድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነቺው ደራሲ ፌቨን ጋሻው ከዚህ ቀደም በራሷ ታሪክ ላይ ተመስርታ የፃፈቺው መፅሐፍ ነው።


 «የንጉሡ ሴት ልጅ» በሚል መፅሐፍ ፅፋ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እንዳተረፈ ይነገርለታል።


ደራሲዋ እንደምትለው ከሆነ፣  በተለይም በአረብ ሀገራት ያሉ ሴት ወገኖች ትልቅ ልምድ እንዳገኙበት   ደራሲዋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ ሰምተናል ።


 አሁን ደግሞ  ደራሲዋ ሁለተኛ ስራቸው የሆነውን "ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለምን?እስከምን" በሚል ርእስ በተፅዕኖ ፈጣሪነት እና መርህ ዙሪያ የተጻፈ  መፅሐፍ ለህትመት አብቅተዋል። 




ሴቶችን የማብቃት ሥራ የሚሠራው የንጉስ ሴት ልጆች የበጎ አድራጎት ድርጅት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሦስት ክልሎች ማለትም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በርካታ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነ ሲሆን ድርጅቱ ሴቶችን ለማብቃት በአንድ ለአንድ የምክር አገልግሎት፣ በቡድን ሥልጠና፣በትምህርት ዕድል እና የአይነት/ቁሳቁስ/ ድጋፍ በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ተረድተናል ።


 አሁን ደግሞ  ደራሲዋ ሁለተኛ ስራቸው የሆነውን «ተፅዕኖ ፈጣሪነት ለምን?እስከምን» በሚል ርእስ በተፅዕኖ ፈጣሪነት እና መርህ ዙሪያ የተጻፈ  መፅሐፍ ለህትመት አብቅተዋል። 


የመፅሐፉ ገፅ ብዛት 166 ነው ተብሏል።


መፅሐፉ በ አምሰት ምዕራፍ የተከፋፈለ ሲሆን በ 300 ብር እንደሚሸጥ ተነግሯል።


መፅሐፉን መሸመት ለሚሹ ከመጋቢት  ሦስት ጀምሮ  በጃፋር መፅሐፍ መደብርና በበይነ መረብ በአማዞን ይገኛል ተብሏል።


መጽሐፉም የፊታችን ሰኞ መጋቢት 2ቀን2016 ከቀኑ 10:00 በስካይላይት ሆቴል ይመረቃል መባሉን ከጋዜጣዊ መግለጫው ተረድተናል።


በምርቃቱ ላይ ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ፣አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ፣አርቲስት ሐረገወይን አሰፋ፣ሲስተር ይርገዱ ሀብቱ እንዲሁም የቢዝነስ አሰልጣኝና አማካሪ ኸይሪያ ዚያድ ይገኛሉ ሲትል ደራሲዋ ነግራናለች ።


(አማኑኤል ክንደያ)



                           -Advertisements-