ቢዝነስ/ዜና
የኮካ ኮላ ቢቭሬጅ አፍሪካ (ሲሲቢኤ) በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የ2025 ከፍተኛና የላቀ ቀጣሪ መሆኑን "ቶፕ ኢምፕሎየር ኢንስቲትዩት" የተሰኘ ተቋም ገልጿል።
ቶፕ ኢምፕሎየር ኢንስቲትዩት የተሰኘው ይኸው ተቋም ባካሄደው ጥናት መሰረት ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ለ2025 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቀጣሪ ደረጃ ካገኙ ስድስት ኩባንያዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስም የገበያ ተደራሽነቱ እያሰፋ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን የሰራተኛ ቅጥርም ገበያው በሚፈልገው ልክ እያሰፋ መሆኑን ተነግሯል።
መንግስት አሐዞች እንደሚያስረዱት ያለፉት ሁለትና ሶስት አመታት የስራ አጥነት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን የሚያስረዱ ሲሆን ይሔንን ችግር ለመቅረፍ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማበረታታት አስፈላጊነት ሲገለፅ ቆይቷል።
ይሁንና የኮካ ኮላ ቢቭሬጅ አፍሪካ (ሲሲቢኤ) በኢትዮጵያ የፈጠረው ከፍተኛ የስራ እድልና የቅጥር አድማስ የ2025 ከፍተኛውን ማእረግ መያዙን ሰምተናል ።
የኮካ ኮላ ቢቭሬጅ አፍሪካ (ሲሲቢኤ) የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳሪል ዊልሰን እንደተናገሩት ሽልማቱ ከሆነም የኩባንያውን አቅም ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸውንና ችሎታ ያላቸው ለመሳብ እንዲሁም በማቆየት ኩባንያው በሰው ሐብት አስተዳደር እድገት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን አቋም ያንፀባርቃል ባይ ናቸው።
በኢትዮጵያ ኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳሪል ዊልሰን እንደገለፁት " እንደ ከፍተኛ ቀጣሪነት ማረጋገጫችን የመማር እና የማደግ ፍላጎት ላላቸው ባለሙያዎች እድል የሚሰጥ ነው" ብለዋል።
ዊልሰን አክለውም በኢትዮጵያ ቀጣይ የገበያ ስኬት እና በተወዳጅ ለማትረፍምና የኮካ ኮላ ምርቶች ተደራሽነት ለማስፋት የተቋሙ ስራተኞች ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ እንዳለም ገልፀዋል።
የኮካ ኮላ ቢቭሬጅ አፍሪካ (ሲሲቢኤ)
በአፍሪካ ከ18,000 በላይ ሰራተኞች እንዳሉት የተገለፀ ሲሆን በአለማቀፍ ደረጃ ከ720,000 በላይ ደንበኞችን እንዳሉት ተገልጿል።
ኩባንያው በ15 ሀገራት ውስጥ የሚሰራ ሲሆን ስድስቱ ቁልፍ ገበያዎች ያሉት ሲሆን የደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሞዛምቢክ እና ናሚቢያ ናቸው።
በተጨማሪም ታንዛኒያ፣ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ዛምቢያ፣ ኮሞሮስ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ እና ማላዊ አገራት ከፍተኛ ገበያ ያለው ኩባንያ መሆኑን ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የኮካኮላ ምርት ተጠቃሚዎች አነስተኛንግድ ቤቶችን ለማገዝ የተለያዩ ስራዎች ሲስራ መቆየቱን የሚታወስ ነው።
በተለያዩ ዙሮችም ነጋዴዎችና ምጣኔ ሐብት አንቀሳቃሾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ እድለኝችን ሲሸልምና ሲያበረታታ መቆየቱንም ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም ።
በአማኑኤል ክንደያ