ዜና/ቴክ
ፋኖስ ቴክ በሳይንስ ሙዝየም ያዘጋጀውን ዝግጅት ወጣቶች ክሪፕቶና ብሎክቼይን እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብር ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ በርካታ ወጣቶች የተሳተፉበት ነበር።
በአለማቀፍ ደረጃ የተጠቃሚዎችንም ቁጥር እየሰፋ መምጣቱን የሚነገርለት የክሪፕቶ ዘርፍ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች እንዴት በአግባቡ መጠቀም ይችላሉ የሚለውን በሰፊው ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።
የፋኖስ ቴክ ድረጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ስንታየሁ እንደገለፁት ከኾነም ድርጅታቸው የብሎክ ቼይን ወጣቶች እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የግንዛቤ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልፀው ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
አቶ ቴዎድሮስ አክለውም፣ ዓለማቀፉ ደረጃ ከፍተኛ ስም ያለው የብሎክቼይን ድርጅት ከሆነው ባይቢት ኩባንያ ጋር በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠረው እድል ለመጠቀም በብርቱ እየሰሩ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች ገልፀዋል ።
በዚሁ ዘርፍ በርካታ ወጣቶች ጥቅም እያገኙበት መሆኑንና ይህም ለአገር ምጣኔ ሐብት እድገት ያለውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ በጉልህ እየተስተዋለ መምጣቱንና በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ የፋኖስ ቴክ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚው አፅንኦት ሰጥተውበታል።
በሳይንስ ሙዚየም የተካሄደው ይኸው ዝግጅት ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የተገኙ የስራ ሐላፊዎች ተሳትፈውበታል።
ለክሪፕቶ ማይኒንግ ስራ የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱና ሃያ በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ በማይኒንግ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የብሎክቸይን ቴክኖሎጂ የጥናት እና ልማት ላይ ባለሞያ አቶ ናኦል ብርሀኑ ተናግረዋል።
አቶ ናኦል አክለውም የክሪፕቶ ዘርፍ ለአገር ኢኮኖሚ እየደገፈ እንደሚገኝ ጠቅሰው የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት አንፃር የተሻለ ጥቅም እያስገኘ መሆኑንና ለወደፊቱም እየተስፋፋ የመሄድ እድሎች እየተስተዋሉ መምጣቱን ገልፀዋል።
መንግሥት ለዚሁ ዘርፍ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደረግለት የፖሊሲ ማእቀፎችን እያሰናዳ መሆኑን እንዲሁም በሕግ እንዲደገፍ እየተሰራበት መሆኑን ባለሞያው ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለምልልስ አስረድተዋል ።
በፋኖስ ቴክ ድርጅትም ለዚሁ ዘርፍ እንዲበረታ እያደረገው ያለውን አስተዋፅኦ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል ።
ይህ እንዲህ እንዳለ ለመገበያያነት በሚውልበት ግዜ ስጋቶች መኖራቸውንና ከወዲሁ መስመር ለማስያዝ እየተሰራበት እንደሚገኝ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የብሎክቸይን ቴክኖሎጂ የጥናት እና ልማት ላይ ባለሞያ አቶ ናኦል ብርሀኑ ተናግረዋል።
ለክሪፕቶ ማይኒንግ ስራ የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱና ሃያ በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች በኢትዮጵያ በማይኒንግ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የብሎክቸይን ቴክኖሎጂ የጥናት እና ልማት ላይ ባለሞያ አቶ ናኦል ብርሀኑ ተናግረዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በበኩሉ
የብሎክቸይን ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ በመግለፅ እንደ ዋና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደርጎ እንደሚቆጠር ገልጿል።
በዚሁ ዘርፍ በርካታ ወጣቶች እየተሳተፉበት መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን መንግሥትም የበኩሉን ድጋፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል ።
የቴክኖሎጂ ሽግግር ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት ያለውን ዲጂታል ኢኮኖሚ አካል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተደጋጋሚ ሲገልፁ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በሳይንስ ሙዝየም በፋኖስ ቴክ ድርጅት አዘጋጅነት የተካሄደው ፕሮግራም በርካታ ወጣቶች የተሳተፉበትና የፓናል ውይይት የተደረገበት መሆኑን ከስፍራው ተገኝተን መታዘብ ችለናል።
በተጨማሪም በርካታ ዘመን አፈራሽ የብሎክቼይን
የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ለእይታ መቅረባቸውንና ያነጋገርናቸው ወጣቶች ግንዛቤዎችን ማግኘታቸውን ነግረውናል ።
በአማኑኤል ክንደያ