አዲሱን አመት ጓደኞቹን ማሰደሰት ይወድ ነበር ፤ ነገር ግን መዋያው ሙዳይ ቤት ነበር ።

 ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት የበአል ምሳ አድርጓል።





ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተው ለወገንዋ ለህዝቧ በሚገዳት ቅን ሰው ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ  ነው። ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት አቃፊ ደጋፊ ለሌላቸው የሀገር ልጆች ለመደገፍ በሚል በተጠነሰሰ ሀሳብ የተቋቋመ በጎ አድራጊ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል ። 


አሁን ላይ "ሙዳይ" ከተመሰረተ 23 አመታት ሞላው።


ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው የ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ዘመን መለወጫን አስመልክቶ በሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት "የምሳ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ" ነበር። ጋዜጠኛ ተሻገር ከኪሱ ቆርሶ "ይቅርብኝ" በማለት አዲሱን አመት ከወገኖቹ ጋር አሳልፏል።


 ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ውስጥ ጥልቀት ያላቸው ርእሰ ጉዳዬች ዙርያ ከሚዘግቡ ( ከሚጠቀሱ) ባለሞያዎች መካከል አንዱ ነው።


ጋዜጠኛ ተሻገር በአይነታቸው ለየት ያሉ ዘገባዎችን በማቅረብ ይታወቃል። በተለይም በአገር ቤት ያሉ ብዙ ጋዜጠኞች የማይደፍሯቸውና እልህ አስጨራሽ የሆኑት የማህበራዊ ዘርፍ ዘገባዎች  ያቀርባል።


ህይወትና በኑሮ ደረጃ ችግርና ጉዳት የገጠማቸው የአገር ልጆች ወገኖችን ወደ ሚድያ እንዲወጡ በማድረግ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ በርካታ ፕሮግራሞችና ዘገባዎችን አጠናቅሮ አቅርቧል ።


በማህበራዊ ዘርፍ ያሉ ዘገባዎችን "ስስ ብልት" ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። አድካሚ  አሰሳ የሚፈልጉ ርእሰ ጉዳዬችን በቀላሉ ፈልቅቆ ማውጣት ይችልበታል።


በኢትዬጵያ መገናኛ ብዙሐን በስራ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲህ ያሉ ስቶሪዎችን ፈልገው ማግኘትና ጥራት ባለው አቀራረብ መዘገብ በጣም ከሚቸገሩባቸው መካከል ይገኙበታል። በዚህ ረገድ ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው ጥርሱ የነቀለበት ሞያ ነው ማለት ይቻላል። 



እንደሚባለውም በጋዜጠኝነት አለም ( ስራ) እንዲህ ያለውን ተሰጥኦ አንድ ሰው ይዞት የሚወለደው ነው የሚሉ ዘርፉን የሚያውቁ ባለሞያዎች አያሌ ናቸው። ጋዜጠኛ ተሻገር በማህበራዊ ዘገባ ዘርፍም በተለይም በተራድኦ (የቻሪቲ ) ስራ ላይ ለረጅም አመታት ካለው ልምድና እውቀት አንፃር ጉዳቱን ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ ልቡም ቶሎ ይነካል።


ለዚህም የሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ በቀረበለት ጥሪ መሰረት "የ2016ዓ/ም ዘመን መለወጫ ካለው ይቅርብኝ ብሎ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት የምሳ ግብዣ አድርጓል "።


የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ እንደምትለው ከሆነም የበአል መዋያ የሚሆን ድጋፍ ባሻትና በቸገራት ጊዜ ጋዜጠኛ ተሻገር ጣሰው" እኔ አለሁልሽ " ብሎ እጁን እንደዘረጋላት ትናገራለች። ሙዳይ ልጆችዋ ደስተኛ ሁነው እንዲውሉ ተሻገር ምክንያት እንደሆናት ስትገልፅም ለጋዜጠኛው ያላት ታላቅ አክብሮት በመግለፅ ነው።


እንዲህ ላለው በጎ አላማና ተግባር መዋእለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ የሀገር ልጆች እንዲበዙም ሙዳይ ምትኩ በጥብቅ ትሻለች። ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ  አከባቢ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ይህ የእርዳታ ድርጅት በየወሩ ከ200 ሺህ ብር በላይ እየከፈለ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሴቶች፣ ህፃናትና አካል ጉዳተኞ ወገኖችን እየደገፈ ይገኛል። 


ከዚህ በቀደሙ አመታት የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር "ለቤት መስርያ የሚውል መሬት" እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ የነበረ ሲሆን ከረጅም አመታት በኃላም በአያትና በቃሊቲ አከባቢ የቤት መስርያ ቦታ መስጠት መቻሉን ሙዳይ ምትኩ ትናገራለች።

U


 በተጨማሪም የከተማ መስተዳድሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ለቤት መስርያነት የሚውል መዋእለ ንዋይ እንደሚሰጡ አልያም እንደሚያፈላልጉ ቃል ገብተው ነበር"። ከንቲባዋ ቃል በገቡት መሰረት ለቤት መስርያ የሚውል ገንዘብ እንዲለግሱም የድርጅቱ መስራች ሙዳይ ምትኩ ጥሪዋን እያቀረበች ትገኛለች።


አሁን ላይ እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ድርጅቱን እጅግ እየፈተነው ይገኛል። ሙዳይ እንደምትለው "ይህን ችግር እንዲቃለልም በየወሩ ለቤት ኪራይ የሚወጣው ፋይናንስ መቀነስ መቻል መፍትሔ ነው ትላለች። ከንቲባ አዳነች በገቡት ቃል  መሰረት የቤት ግንባታው ቢፈፀም ድርጅቱን እየደጋገመው ያለውን እንደሚያቃልል ሙዳይ ትናገራለች።


የመገናኛ ብዙሐን በአያት አከባቢ የተሰጠውን 2000ካሬ ሜትር መሬትና በቃሊቲ አከባቢ ያለውን 2000 ካሬ ሜትር መሬት፣ በአጠቃላይ 4000 ካሬ ሜትር መሬትእንዲገነባ አስፈላጊውን ውትወታ እንዲያደርጉ የሚጠበቅባቸውን ሐላፊነት እንዲወጡ ይጠበቃል።


ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከከተማ መስተዳድሩ የተረከበውን መሬት እንዲገነባለት ባለሀብቶች መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያቀርቡና እንዲደግፉ ጥሪ እየቀረበ ይገኛል።