በሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው "ሰላም በብዝኀ ሃይማኖት ማህበረሰብ" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን ቅዳሜ 'ለት ሊመረቅ መሆኑን ተሰማ

 ዜና




የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ በሆኑት ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የተፃፈው በሰላም ግንባታ ላይ የሚያተኩረው "ሰላም በብዝኀ ሃይማኖት ማህበረሰብ" የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን ሚያዚያ 4 ይመረቃል ተብሏል ።


መፅሐፉ አስራ ሶስት ምዕራፎችን የያዘና ሀይማኖታዊ የግጭት አፈታት ላይም ትኩረት ያደረገ በቀጣይ ግጭትን በሀይማኖታዊ ስርአት መፍታት እንዲቻል የሚያግዝ ነው ተብሏል።


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በረዥም የትምህርት፣ የአገልግሎት እና የመሪነት ኃላፊነት ያካበቱትን ዕውቀት እና ልምድ በሰላም ግንባታ ዙርያ ለሚደረግ ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር፣ ግብአትነት ይውላል የሚል እምነት ተጥሎበታል።


መጽሐፉ በሀገራችን ሰላምን ለማስፈን የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ጥረት በብዙ የሚያግዝ እና በሰላም ትምህርት እና ስልጠና ላይ ለተሰማሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዋቢ ሆኖ  ሊያገልግል እንደሚችል ተነግሯል ።


 በተጨማሪም፣ በሰላም ግንባታ ላይ ለሚሰሩ ተቋማት እና ግለሰቦች ከፍተኛ ጥቀም እንዲሰጥ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ መሪዎች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል ተብሏል ፡፡


መጽሐፉ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን ወደ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ተርጉሞ ማሳተም፤ ሰላምን አስመልክቶ ሀገር ዓቀፍ ወርክሾፖች ይቀርባል ተብሏል።


ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በትውልድ ውስጥ የሰላም ዕሴትን ለማስረጽ እንዲረዳ መጽሐፉን ለትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ማዕከላት፣ ዩኒቨርሲቲዎች በነፃ እንደሚሰራጭ ተገልጿል ።


ለሕዝብ ተቋማት በነጻ ማሰራጨት፤ መጽሐፋ ያነሳቸውን የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ የምክክር፣ የበይነ ሃይማኖት ውይይትና የዓመጽ ጠልነት ዕሴቶችን ያጎለብታል ብለዋል።


ሰላም በብዝኀ ሃይማኖት ማህበረሰብ የተሰኘው  ይኸው መፅሐፍ  የፊታችን ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ መሪዎች እና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት ይመረቃል ፡፡


በአማኑኤል ክንደያ


                     ADVERTISEMENTS