ሳፋሪኮም ኩባንያ በኢትዮጵያ አዲስ ስራ አስፈፃሚ መሾሙ አስታውቋል



በአማኑኤል ክንደያ



ሳፋሪኮም ኩባንያ በኢትዮጵያ አዲስ ስራ አስፈፃሚ መሾሙ ተናግሯል ።


ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርቡ ለቅቀዋል ሲባል የነበሩትን የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመተካት አዲስ የስራ አስፈፃሚ መሾሙን ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ተናግሯል ።


ቤልጂየማዊዉ አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ዊልያም ቫንሀለፑተን የሚሰኙ ሲሆን የቀድሞዉ ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳን በመተካት የተሾሙ መሆኑ እወቁልኝ ብሏል።


 አዲሱ ስራ አስፈፃሚ በዘርፉ ትልቅ እዉቀትና የ 25 አመታት ልምድ ያላቸዉ ባለሞያ ናቸው። 


ኩባንያው በኢትዮጵያ ከ 900 በላይ ሰራተኞች ያሉት መሆኑንም አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።


ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት ትርፍ አግኝቷል ለማለት ከባድ ንኑ ያሉት ስራ አስፈፃሚዉ በቀጣዮቹ ሁለትና ከዛ በቀረቡ አመታት ዉስጥ የትርፍ መንገዱን እንደሚያገኘዉ ጠቅሰዋል።


በአሁኑ ሰዓት ከ 2 ሺህ በላይ የቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ይህንን ወደ 7 ሺህ ለማሳደግ ማቀዱን ተናግረዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት 35 በመቶ የኢትዮጵያን ክፍል በኔትወርክ መሸፈን መቻሉን ያነሱ ሲሆን ይህንንም በሁለት አመታት ዉስጥ ከ 80 በመቶ በላይ ለማሳደቅ መወጠኑን  ተሰምቷል።


ኩባንያው በሁለት አመታት ዉስጥ የኔትወርክ ሽፋኑን ከ 80 በመቶ በላይ ለማድረስ አቅጃለሁ ማለቱን ሰምተናል።


ኩባንያው ፣ በኢትዮጵያ ተስፋ ያለዉ አቅም ያለዉ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቅርቡ አገልግሎት መስጠት በጀመረዉ ኤም ፔሳ ዲጂታል የገንዘብ መላላኪያ ስርዓትም መልካም ጅማሮ ማሳየቱን ጠቅሰዋል። 


ተቋሙ በቀጣቶቹ ሁለት አመታት 500 ለሆኑ ሰዎች ቀጥተኛ የስራ እድ እንደሚፈጥርም አስታዉቋል።



                       -Advertisment-



(ንጋት ፕሬስ )