Photo : Ahmed shedi state minster of finance and exim bank chairman m/r wefline
በፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የኢትዬጵያ ልኡክ ቡድን "የብድር ክፍያ፣ ለፕሮጀክቶች በሚለቀቅበት ሁኔታዎችና የብድር ክፍያ ሽግሸግ" በተመለከቱ ጉዳዬች ዙርያ ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የቻይና መንግስት በተደረገ ጥሪ መሰረት በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ ያለው አህመድ ሽዴ የሚመራውና በክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታን የያዘው የገንዘብ ሚንሰቴር ልዑካን ቡድን የቻይና አበዳሪ ተቋማት በኢትዮጵያ ማዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ከፍተኛ የልማት ስራዎች በመስራት ላይ ካሉ እንዲሁም ወደፊት መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ከሚሹ የኩባንያዎች ጋር እጅግ ፍሬያማ ውይይት እያደረጉ መኾኑን ሰምተናል፡፡
ከነዚህም መካከልም ከቻይናው ኤክሲም ባንክ ሊቀመንበር ሚስተር ውፍሊን እና ከባንኩ ኃላፊ ዋኑ ጋር ላለፋት ዓመታት በባንኩ የተያዘው የብድር ክፍያ ለፕሮጀክቶች በሚለቀቅበትና የብድር ክፍያ ሽግሸግ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ልኡኩ ከባንኩ የስራ ኃላፊዎች አበረታች ምላሽ አግኝቻለኹ ብሏል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ከቻይና ልማት ባንክ ሚስተር ዋንግ ዎልዶንግ ከምክትሎቻቸው እና ከተለያዩ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የብድር ክፍያ ማራዘሚያ ድርድር በቶሎ በሚቋጭበትና ባንኩ በቀጣይ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ከዚህም ሌላ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ካፈሰሱና ወደፊት በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ስራዎች መሳተፍ ከሚፈልጉ ኩባንያዎች የስራ ኃላፊዎች ጋር የተናጥል ውይይት ተደርጓል ተብሏል፡፡
ከእነዚህም መካከልም ከቻይና መንገድና ድልድይ ኮንስትራክሽን ድርጅት (CRBC)፣ CGCOC እና CGGC ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ ልማት ለሚሳተፋ የቻይና ድርጅቶች የሚደረገው የመንግስት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ለተሳተፋ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
(ንጋት ፕሬስ)


