በኢ- ኮሜርስ ዘርፍ የተሰማሩ ከ20 በላይ አገር በቀል ኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ሀሳባቸውን የሚያቀርቡበት ፕሮግራም መካሄዱ ተነገረ





 በኢ- ኮሜርስ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን የሚያሳዩበት መርኃ ግብር በአዲስ አበባ  ተካሄደ


የኢ-ኮሜርስ ማሳያ መርኃ ግብሩ የቬንቸር ሜዳ ይሰኛል።


በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎችን እና የነባር የኢኮሜርስ ላይ የተሳተፉ ድርጅቶችን እድገት ለማፉጠንና  በሀገር ውስጥ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በኢኮሜርስ ውስጥ ለማሳተፍ የሚያግዝ የቬንቸር ሜዳ የማሳያ ቀን 2023 የተሰኘ ፕሮግራም  በኢሊሌ ሆቴል ተካሄዷል።




ከግንቦት 2022 ጀምሮ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኢ.ሲ. አዲስ ጋር በመተባበር በኢኮሜርስ ሶልሽን ዘርፍ አዳዲስ ፈጠራን በኢንኩቤሽን እና በአክሰለሬሽን ድጋፍ ለማጎልበት ቬንቸር ሜዳ የተባለ ፕሮግራም  መካሔዱን ተመልክተናል።


ይኸው መርኃ ግብሩዠር  ሁለት ዋና አላማዎችን ያሉት ሲኾን - ማለትም በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎችን እና የነባር የኢኮሜርስ ላይ የተሳተፉ ድርጅቶችን እድገት ለማፉጠንና  በሀገር ውስጥ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በኢኮሜርስ ውስጥ ለማሳተፍ ሲሰሩ እንደቆዩ ናቸው ተብሏል።


በዚህ ፕሮግራም ያለፉ 20 ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የመንግስት አጋሮች ፣ ባለሙያዎች፤ ለባለሀብቶች እንዱሁም ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የፈጠራ ኃሳቦቻቸው አሳይተዋል።




በተጨማሪም ከኢኮሜርስ ሶልሽን ዘርፍ ላይ የፓናል ውይይትና ነበር።


"ቬንቸር ሜዳ" በአለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የኢ-ኮሜርስ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሳተፉ እንግዶችን የሚደግፍ መኾኑን ሰምተናል።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)