ማህበራዊ /ዜና
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎች ለመስጠት የሚያስችል ወደ 31 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶች ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ ማድረጉ ተመልክተናል።
ባንኩ በተያዘው በጀት አመት ለማህበራዊ ሐላፊነት ለመወጣት የሚያስችል 29 ሚልየን ብር መዋእለ ንዋይ ፈስስ ማድረጉን የህክምና ቁሳቁሶችን ለማዕከሉ በሚያስረክብበት ጊዜ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ወደ ማዕከሉ በመምጣት ባደረጉት ጉብኝት፣ ከጤና ባለሞያተኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት መሠረት ማዕከሉ የቀዶ ህክምናውን ለመስጠት እንዳይችል ያደረጉትን ችግሮች በመረዳት የማዕከሉ የህክምና ባለሙያዎችን አነጋግረው ነበረ።
ዶክተር የሀንስ የልብ ህክምና ማዕከሉ ያሉበትን ችግሮች በመረዳትና ከአቅም በታች እንዲሰራ ያደረጉት ምክንያቶችን በመገንዘብ ማእከሉ የነበሩበትን የህክምና ቁሳቁስ ችግሮች ማወቅ በመቻላቸው ባንኩ የማዕከሉን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ድጋፍ ለማድረግ በወቅቱ ቃል ገብተው ነበር።
የባንኩ ሐላፊው ዶክተር የሀንስ በገቡት ቃል መሠረት ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ/ም በማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ተገኝተው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ለቀዶ ህክምና የሚያገለገሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን በማዕከሉ ተገኝተን ታዝበናል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው እንደተናገሩት ከኾነም - ባንኩ በሀገሪቱ ብቸኛው የፖሊሲ ባንክ እንደመሆኑ መጠን ሀገራዊ ልማቶችን በማገዝና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ መወጣት እንዳለበት በሚገባ ይረዳል ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ ሰምተናል ።
ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተገኘው ድጋፍ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎች ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።
ባንኩ ለልብ ቀዶ ህክምና ማዕከል ባደረገው ድጋፍ መሠረትም በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ወረፋ የሚጠብቁ በርካታ ታካሚዎችን እንግልት እንደሚቀንስና የተቀላጠፈ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ ተረድተናል።
የኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል በቂ የህክምና ቁሳቁስ ካገኘኹ በአመት ከ1500 በላይ ህፃናት የልብ መስጠት የሚያስችል አቅም አለኝ ብሏል።
በቁሳቁስ ርክክብ ስነስርዓት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የልብ ህክምና ማዕከል አምባሳደር በመኾን እየሰራች የምትገኘው አርቲስት መሠረት መብራቴ ተገኝታለች።
አርቲስት መሠረት መብራቴ የተበረከተው የህክምና ቁሳቁስ ዙርያና ለማእከሉ ስለምታከናውናቸው ጉዳዬች ሐሳቧን አቅርባለች።
መሠረት ለሁለቱም በጥምረት አምባሳደር ሆና እያገለገለች ትገኛለች።
( ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)


