በኢትዮጵያ ብቸኛው የውጭ የሊዝ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ሰምተናል

 



በኢትዮጵያ ብቸኛው የውጭ የሊዝ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ሰምተናል። ኢትዮ ሊዝ የተሰኘው በውጭ ሰዎች የተያዘው ኩባንያ ከኢትዮጵያ ለመውጣት ያስገደዱት ምክንያቶች፣ ኹሉም የሊዝ ስምምነቶች ቁርጥ ክፍያ በውጭ ምንዛሬ ሳይኾን በብር መክፈል እንዳለባቸው እንዲኹም የውጭ የሊዝ ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ ባንክ ብር እንዳይወስዱ የሚከለክሉት አዲስ መመሪያዎች መውጣቱን ተከትሎ መኾኑን የኩባንያው ስራ አስፈፃሚ ዳግሎ አረጋግጠውልናል። ኩባንያው ከአምስት ዓመት በፊት ከብሄራዊ ባንክ ባገኘው ፍቃድ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ የተሠማራ የመጀመሪያው የውጭ የሊዝ ኩባንያ ነበር። ኩባንያው፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ትራክተሮችንና ሌሎች እቃዎችን በሊዝ ያከራይ ሲያከራይ ቆይቷል። ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪም የህክምና መሳርያ ዕቃዎች በሊዝ ማከራየት ጀምሮ እንደነበርም ይታወሳል። የኩባንያው መቀመጫ ኒውዮርክ የሚገኘው የአፍሪካ የንብረት ፋይናንስ ኩባንያ ነው።


(ንጋት ፕሬስ)