ቢዝነስ /ዜና
ኖህ ሪል እስቴት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ያስገነባቸውን 754 የመኖሪያ ቤቶች ምርቃት ስነ-ስርአትና 10ኛ ዓመቱን የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት አክብሯል።
ኖህ ሪል እስቴት ባለፉት አስርት ዓመታት 8 ሺ በላይ ለሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በታማኝነት፣ በሰዓቱ እና በቃሉ መሰረት ያስረከበ ሲሆን ይህ ጉዞ ኩባንያውን በኢትዮጵያ የቤቶች ልማት ዘርፍ ቁልፍ ተዋናይ ሆኖ እንዲቀጥል እንዳስቻለው ተገልጿል።
ኩባንያው ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬትም ትልቅ አስተዋዕዖ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግሯል።
የኖህ ሪል ኢስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ንፁህ አውግቸዉበዛሬው ዕለት በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን የመኖሪያ መንደር በይፋ ሲያስመርቅ ባለፉት አስርት ዓመታት የስኬት ጉዞአችን የምናከብርበት፣ እንዲሁም ወደፊት በአብሮነት ለተሻለ ሥራ ቃልኪዳናችንን የምናድስበት ነው ብለዋል።
ኖህ ሪል እስቴት የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በጊዜው እና በጥራት ገንብቶ በማጠናቀቅ በደንበኞቹ ዘንድ አመኔታን ያተረፈ ተቋም ነው ሲሉም አክለዋል።
ኩባንያው በ2020 ዓ.ም ፣ 30 ሺ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ትልቅ ራዕይ የሰነቀ ሲሆን ፣ የመኖሪያ ቦታዎችን ወደ ሚሊዮኖች ካሬ ሜትር ለማስፋፋት ማቀዱም ተነግሯል።
በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለማልማት ከታቀደው 3 ሚልየን ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ሲሆን 1ሚልየን ካሬ ሜትር ያህል ደግሞ የንግድ ማእከላት ለመገንባት ይውላል ተብሏል ።
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀከቶች የኖህ ሪል ስቴት ለላቀ ትጋት ቀጣይነት ማሳያ እንደሆኑ ተነግሯል።
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ እንደተገለፀው የኖህ ታላቅ ስኬት ዋነኛ ማሳያው 31 ፕሮጀክቶች በጥራት እና በተቀመጠለት ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉ ነው። አሁን ላይ በርካታ በመካሄድ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉት ኩባንያው ከፕሮጀክቶች መካከል በጉርድ ሾላ፣ በሰሚት፣ በቦሌ ፣ በፍላሚንጎ፣ በቀበና እና በእንቁላል ፋብሪካ ያሉ ግንባታዎች በመፋጠን ላይ ይገኛሉ።
ኖህ ሪል እስቴት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ያስገነባቸውን 754 የመኖሪያ ቤቶች ምርቃት ስነ-ስርአትና 10ኛ ዓመቱን የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በዛሬው እለት አክብሯል።
(ለንጋት ፕሬስ ንጉሴ መንገሻ)


