የቤት ኪራይ ዋጋ ንረትና አዲስ አበባ

የቤት ኪራይ ንረት

- አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሐገሪቱ ከተሞች የቤት ኪራይ እየናረ በተለይም መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ለጣቢያችን የሚላኩ ጥቆማዎች ያመላክታሉ። የአዲስ አበባ መስተዳደር በየጊዜው አከራዮች የቤት ኪራይ እንዳይጨምሩና ተከራይን እንዳያስወጡ መመሪያ ቢያወጣም ተግባራዊነቱ ግን እምብዛም እንደሆነ ተከራዮች ስሞታቸውን ነግረውናል። በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ አከራዮች ቤቱ ለሌላ ሥራ ይፈለጋል፣ ቤተሰብ ከውጭ መጥቶብኛል፣ ለእድሳት ወዘተ በሚሉ ሰበብ አስባቦች ተከራዮችን እንደሚያስወጡ  እንዳሉ ይነገራል። የከተማዋ አስተዳደር በቤት ባለቤቶች ላይ ያወጣው አዲስ የንብረት ባለቤትነት ታክስ ምጣኔም ጫናው በይበልጥ በተከራዮች ጫንቃ ላይ የሚወድቅ በመሆኑ ችግሩን እንዳወሳሰቡት ነው። በተለያየ ጊዜ ተገንብተው ያለቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶችም የማጠናቀቂያ ሥራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ወደ ባለቤቶች ባለመተላለፋቸው ሳብያ ችግሩን ይበልጥ እንዳከበደው ይነገራል። በየአካባቢያችሁ ያለው የቤት ኪራይ ሁኔታ እንዴት ነው? ለችግሩ ይበጃል የምትሉት መፍትሄስ? ተወያዩበትና ሀሳባችሁን ስደዱልን ። 

(ንጋት ፕሬስ እለኒ ጋሻው )