የብርሃን ባንክ ፕሬዝዳንት ግሩም ፀጋዬ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተሰማ


               ፎቶ :- ግሩም ፀጋዬ

ብርሃን ባንክ ፕሬዝዳንት ግሩም ፀጋዬ ሀሙስ ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በፃፉት ደብዳቤ በግል ምክንያት ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ጥያቄ አቅርበዋል። የባንኩ ቦርድ የግሩምን ጥያቄ የተቀበለ ሲሆን በባንኩ የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ምንም ዓይነት ክፍተት እንዳይፈጠር በምትካቸው የኦፕሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ሰለሞን አሰፋን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡  የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ  ለወደፊት ባንኩን በቋሚነት የሚመሩትን ፕሬዝዳንት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያሳውቅ ሲሆን፤ የባንኩን አመታዊ አፈጻጸምና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በሚያካሂደው ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ስብሰባ እንዲሁም በባንኩ ማህበራዊ ድህረ-ገፅ አሳውቃለኹ ማለቱን ከባንኩ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክተናል። 




(ንጋት ፕሬስ)