"የኛ ምርት" የተሰኘ አነስተኛና መካከለኛ አገር በቀል አምራች ኢንተርፕራይዞች በአንድ ጣርያ ስር የሚገናኙበት ባዛርና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሔድ ነው ተባለ

 ቢዝነስ/ዜና

         
         ፎቶ:- ነብዩ ለማ የፕራና ኤቨንትስ ማ/ዳይሬክተር



የኛ ምርት ባዛርና ኤግዚቢሽን በአገር ውስጥ ያሉ አምራች ኢንተርፕራይዞችና የመንግሥት የልማት አጋር ድርጅቶች የሚሳተፉበት "ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛ እንሸምት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲኾን "የኛ ምርት" የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ለማወቅ ችለናል።


የኛ ምርት ባዛርና ኤግዝቢሽን ዋና አላማ በምርት ትውውቅ፣ገበያ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በልምድና መረጃ ልውውጥ የተሻለ አቅም መፍጠርና ዘርፉ ያለበትን እድገት ለማሳየትና ለማስተዋወቅ መኾኑን ተረድተናል።


በአገር ውስጥ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ባዛር ከ ታህሳስ 03- 07 2016 ዓ/ም ድረስ  በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በድምቀት የሚካሄድ መኾኑን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና አዘጋጁ ፕራና ኤቨንትስ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል ።


 ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ "ዝግጅቱ ተወዳዳሪ የኾኑ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መፍጠር ውጥን ያለው መኾኑን" አዘጋጆቹ ሲናገሩ ተደምጠዋል።


     ፎቶ:- አለባቸው ንጉሴ የኢንተርፕራይዝ ልማት ዳይሬክተር


የኛ ምርት ባዛርና ኤግዝቢሽን ዋና አላማ በምርት ትውውቅ፣ገበያ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በልምድና መረጃ ልውውጥ የተሻለ አቅም መፍጠርና ዘርፉ ያለበትን እድገት ለማሳየትና ለማስተዋወቅ ያለመ መኾኑን ከመግለጫው ተረድተናል።


ባዛሩና ኤግዝቢሽኑ ማዘጋጀቱ አስፈላጊ የኾነበት ምክንያት ሲናገሩ እንደሰማነው የውጭ ምንዛሪ ማስገኘትን ጨምሮ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩትን የአገር ውስጥ ምርቶችን ይበልጥ ለማስተዋወቅና ማበረታታት ጨምሮ ለውጭ  ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን በማስተዋወቅ ለአገር ምጣኔ ሀብት የሚሰጡት ጥቅም ለማሳደግ ውጥን መያዙን ነው ። 


እንዲኽ ያለውን ባዛርና ኤግዚብሽን "በአገራቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ" ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲኾን ከ100 በላይ በጨርቃጨርቅ፣ ቆዳ፣ ኬሚካል፣አግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አምራቾች  የሚሳተፉበት መኾኑንም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ ሲናገሩ ሰምተናል ።  በመርኃ ግብሩ ላይ ከ50,000 ያህል ገዥዎችና ጎብኚዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ውጥን ተይዞለታል።




ባዛሩና ኤግዚቢሽኑ ለማዘጋጀት በአገራቀፍ ደረጃ ከ15 በላይ ተወዳዳሪ ኩባንያዎች ለውድድር ቀርበው ባስገቡት ንድፈ ሐሳብ መሠረት የተጫረቱ ሲኾን በተደረገው  ልየታ መሠረት ፕራና ኤቨንት የተሰኘው አገር በቀል ኩባንያ ባቀረበው ፕሮፖዛል ብቁ ሁኖ በመገኘቱ ዝግጅቱን እንዲያዘጋጅ ፍቃድ ሊሰጠው መቻሉን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ  ዳይሬክተሩ አለባቸው ንጉሴ አስረድተዋል።


የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኃላፊው አለባቸው አክለው እንዳብራሩት ፕራና ኤቨንትስ ባለው ልምድ ፣የቴክኒክ ብቃትና ገንዘብን አብቃቆቶ በመጠቀም ደረጃ ባለው የካበተ ልምድ መሠረት ለአምስት ቀናት በስካይ ላይት ሆቴል የሚከናወነው ባዛርና ኤግዚቢሽን ይሁንታ ሊሰጠው መቻሉን ከኃላፊው ንግግር ለመረዳት ችለናል ።

 

የፕራና ኤቨንት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ በበኩላቸው ባዛሩና ኤግዚቢሽኑን አስመልክተው ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ በሌሎች አገራት ያለውን ልምድ ጠቅሰው ፣ እንዲህ ያለውን ባዛርና ኤግዚሸን ዝግጅት ማዘጋጀቱ አምራች ኢንተርፕራይዞች በአገር ምጣኔ ሀብት እድገት ላይ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መኾኑን አፅንኦት ሰጥተው አብራርተዋል ።



 እንደ ነብዩ ለማ ማብራርያ በተለይም መካከለኛና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች  አብዝተው ከሚፈተንባቸው መካከል የግብአት፣ ገበያና የሰው ኃይል አቅርቦት ለመፍታትና ችግር ለመፍታት ብሎም  በአገር ውስጥ ያሉ አምራቾች የገበያ ትስስር በመፍጠር ከፍተኛ እገዛ በመፍጠር ለዘርፉ እድገት የራሱን ሚና እንደሚጫወት በመግለጫው ሲናገሩ ተደምጠዋል ።


የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በበጀት አመቱ ከያዛቸው መሠረታዊ ዕቅዶች መካከል ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ የመተካት ውጥን ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንዳለም ዳይሬክተሩ አለባቸው ንጉሴ ሲናገሩ ሰምተናል።


በኢትዮጵያ ውስጥ በአኹን ላይ ከ26 ሺህ በላይ አነስተኞና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በመላው አገሪቱ ይገኛሉ ተብሏል። በተቋሙ መሪ ልማት ዕቅድ እንደተጠቀሰውም ከፍተኛ ካፒታልና የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ሚጠይቀው ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ  በማሸጋገር ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መኾናቸውን ተጠቅሷል።  


በተያዘው በጀት አመትም ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ አሁን ላይ ከደረሰችበት የውጭ ምንዛሪ የገቢ ደረጃ 405.6 ቢልየን ወደ 900 ቢልየን ለማድረስ ውጥን ይዛ እየተንቀሳቀሰች መኾኑን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያገኘነው መረጃ ይናገራል ።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)