ለ22 ቀናት የሚቆየው ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ተከፍቷል

 ዜና /ቢዝነስ 





ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ያዘጋጀው ለ22ቀናት የሚቆየው 33ኛው ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል ተብሏል። 


በዝግጅቱ ላይ ከ500 በላይ የንግድ ተቋማት እና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎቢኚዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


በዚህ የንግድ አውደ ርዕይ   ላይ በየዕለቱ ታዋቂ አርቲስቶች የሚሳተፉበት የሙዚቃ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ የሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውግ ጀማነህ ገልጸዋል።



 በገና ባዛር ላይ የቤት ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የህፃናትና የአዋቂ አልባሳት ፣ የስጦታ ዕቃዎች የተለያዩ ምርቶች ቀርበዋል ተብሏል።


በተጨማሪም ለበዓል የሚሆኑ የአስቤዛ ምርቶች  ለሽማቹ በአምራች ዋጋ ያለገደብ ይቀርባሉ ነው የተባለው።


ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና   የተመሠረተበትን 25ኛ የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን በማክበር ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል።



(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)