ፒያሳ ለምን አረጀች ?

 


እኔ ሳድግ ደግሞ ፒያሳ  ዋነኛው የአዲስ አበባ center  ነበር። ኮሚኒስቶቹ ቤቶቹን ሁሉ ወረሱና ፒያሳን የቀበሌ ቤት ሰፈር አደረጉት። የመንግስት ቤት ደግሞ የማንም ስላልሆነ የሚጠግነው፤ የሚያድሰው፤ ቀለም የሚቀባው የለም። ስለዚህ  ወታደሮችና እነሱን የተኩት ከገጠር የሚመደቡ ከንቲባዎች ፒያሳን አስረጁት አቆሸሹት አበከቱት።

  

እኔ ዩኒቨርስቲ ልጨርስ ስል ከተሜው ወደ  ስታዲዮም ካካባቢ ሸሸ፣ ስታዲዮም ቶታል፤ ላሊበላ ሬስቶራንት፣ ጊዮን ዩኒቲ ካፌ፤ ፎር ኮርነርስ ክለብ (Four Corners) የሚባል እነ ሀመልማል ይዘፍኑበት የነበረ ጋንዲ አካባቢ ያለ ክለብ፤ አንባሳደር  ትያትር ስር ያለ ክለብ ፒያሳን ተክቶ ወደ ስታዲዮም ሰዉን አመጡት።  ከዛ ካገር ወጥቼ ስመለስ ቦሌ መንገድ ደግሞ የኢትዮጵያ Oxford street ሆኖ አገኘሁት።


ታድያ ለፒያሳ ማርጀት ተጠያቂው ማነው? ለ 50 አመታት የመሩት ከንቲባዎች አይደሉም።  

እኛ ስለቅርስ እውቀታችን ውሱን ነው። ገና አልገባንም ስለዚህ እያጠፈ የታሪክ መሳቂያ እየሆንን ነው። አሁን እንኳን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ መሀበር አመሪዎች ብዙዎቹ በኢትዮጵያ የነበሩ የእንግሊዝ የኢሮፕ አንባሳደሮችና የሪቻርድ ፓንክረስት ቤተሰቦች ናቸው። እነሱ ናቸው ቅርስ እየመዘገቡ እባካችሁ አሁን ሊገባችሁ አይችልምና አታፍርሱት እያሉ የሚጮሁት።  ብዙም ህንጻ ያዳኑት።


እስቲ ፒያሳ ያለውን Castelle restaurant እንሂድ። አሮጌ ቤት ነው ነገር ግን ኢትዮጵያን የረገጠ የሆሊውድ ፊልም ሰሪ እነ አንጆሊና ጆሊ ፣ ዊል ስሚዝ፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እነ ጆርጅ ቡሽ የብሪቴን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቶኒ ቢሌር፣ የደቡብ አፍሪካው ታምቦ ማኬባ እዛ ቤት በልተው ፎቶ ተነስተው ፎቶዋቸን ተለጥፎ እናያለን።


 ለምን ይህንን አሮጌ ቤት ከነሸራተንና እና ከሌሎቹ ዘመናዊ ሬስቶራንት መረጡ? ምግብ ሳይሆን ታሪክ ነው የሚሸጠው።


ፒያሳ ያረጀው ደርግ ወርሶ የቀበሌ ቤት ስለተደረገው ነው። ሌላ ምንም ምክንያት የለም።  ባለቤት የሌለው ማንኛውም ቁስ ያረጃል። ያልታደሰ ንብረት ያረጃል ይጠፋል። የፒያሳ ማርጀት ስርአቶቹ ናቸው ተጠያቂዎቹ። እንድ ወር አንድነት ፓርክ ውሀ ባይጠጣ ባይታረም ባይቀባቡት ሳሩ ይደርቃል፣ ብርቱ ይዝጋል ሰው ገብቶ በፌስታልና በውሀ ላስቲክ ይሞላዋል ወይንም ይጸዳዳበታል።


 እኔ የምለው ስለ ቅርስ ጥቅም ለማወቅ ብዙ ማደግ ይጠይቃል። አብረሀም ሞስሎው (Abreham Maslow) ሰው ወደ Self-Actualization ለመድረስ ብዙዎቹ ፍላጎቶቹ እያማላ ማደግ አለበት ይላል።


ስለዚህ ታሪክ ባለማወቅ አፍርሰን የተጨናነቀና አስቀያሚ ህንጻ መደርደር አያስከብረብንም።  እንደውም አላዋቂነታችንን በወርቅ ቀለም ጽፎ ማለፍ ነው።


(ያሬድ ኃይለመስቀል)