የድምፃዊ አስቻለው ፈጠነ "አስቻለ" አልበም ሊለቅ ነው ተባለ

ኪን/ዜና 


እንሆ ሙዚ-ቃል


 የአስቻለው ፈጠነ -አስቻለ-የተሰኘውን ሙሉ አልበም ነገ ለአድማጮቹ ያደርሳል።


ከኹለት አመታት በላይ የፈጅውና እልኽ አስጨራሽ ስራ ነበር የተባለው የአስቻለው ፈጠነ አልበም በርካታ የኪያንያን የጥበብ ሰዎቻቸው አሻራቸውን ያሳረፉበት አልበም ሊለቀቅ ነው ።

ዘመን አፈራሽ ኢትዮጵያዊ ሙዚቃ ነው ማለት  ይቻል ይኾናል ። አልበሙ ስብጥር ነው።


አልበሙ ነገ ጥር 2/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ በBirbaux ሪከርድስ እንደሚለቀቅ ሠምተናል።

አዘጋጆቹ እንደውም አለማቀፍ ደረጃ የተሰራ አልበም ነው ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል።




አድማጮች እስኪ ሙዚቃውን አጣጥሙትና አስተያየታችኹን አጋሩን ።


አስቻለው ፈጠነ በሰጠው መግለጫው ላይ እንደተናገረው፣ ይህን ሙዚቃ  ስንሰራው ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ አልበሙ በትግረኛ፣ ኦሮምኛ፣ቤንሻንጉል እና አገወኛ ቋንቋን የተሰሩ ሙዚቃዎች አሉት ብሏል።


የፊልም ባለሙያው ሰውመሆን ይስማው/ሶሚክ ሙዚቃውን ፕሮዲውስ አድርጎታል። 


ሙሉ አልበም በውስጡ አሰራ አራት ሙዚቃዎች ይዟል።


ዘጠኙ ሙዚቃዎች ሰርቶና ቀንብቦ ያቀናበረው በቅርቡ በሞት ለተለየው ለአቀናባሪ እና ለሙዚቃ ባለሙያው ለእስራኤል መስፍን መታሰቢያ ይሁንልኝ ሲል ሙዚቀኛው አስቻለው ፈጠነ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።


ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፍ እድገት ያለንን አመለካከት የሚያሻሽል ነው ተብሎለታል እስኪ ስሙት።


(ንጋት ፕሬስ )