የኮካ-ኮላ ምርቶችን አምራች የሆነው ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ ለ130 ንግድ ቤቶች የፍሪጅ ሽልማቶችን አበረከተ

ቢዝነስ /ዜና




 የኮካ-ኮላ ምርቶችን አምራች የሆነው ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ የተሰኘው ኩባንያ ለ130 ንግድ ቤቶች የፍሪጅ ሽልማቶች ማበርከቱ ተሰማ።


ይኸኛው የሽልማት ሰነ ስርአት ለሦስተኛ ዙር የተካሔደ ነው።


 ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ የተሰኘው ይኸው ኩባንያ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ/ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቅፅር ጊቢ አዳራሽ ባካሔደው የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርአት ለ130 ንግድ ቤቶች ፍሪጆችን መሸለሙ አስታውቋል ።


ኩባንያው በኢትዮጵያ ሽያጭ ስርአቱን ለማስፋፋትና ለማበረታታት እንዲሁም የንግድ አቀላጣፊዎችና ባለቤቶችን ለመደገፍ በሚል ለሶስት ወራት የቆዮ "ይግዙ፣ይሽጡ፣ ይሸለሙ" የተሰኘ ፕሮሞሽን ሽልማት ማካሄዱን ተረድተናል።


          photo; የእጣ አወጣጥ ስነስርዓት ሲከናወን


ሽልማት የተበረከተላቸው በአዲስ አበባ ከተማ  ላሉ የንግድ አቀለጣጣፊዎች መኾናቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐኖች ባካሄደው የማጠናቀቅያ መርሐግብር ተገኝተን ተመልክተናል ።


ኩባንያው ለንግድ ድርጅቶች 7 ሚልየን ብር መዋእለ ንዋይ ፈስስ በማድረግ ከ 200 በላይ ፍሪጆችን ለሽልማት አቅርቦ ሲያወዳድር ቆይቷል።


ፕሮሞሽኑ የንግድ ስራውን ለማቀላጠፍ እንዲረዳቸው፣  በዋነኝነት ደግሞ ከድርጅቱ ጋር ዘላቂ  ግንኘነት ለመፍጠር ብሎም ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ መርኃ ግብር መኾኑን ሲናገር ሠምተናል።




 ሲሲቢኤ- ኢትዮጵያ በሶስት ዙር በውድድሩ 75 ሺ ነጋዴዎች ያህል ይሳተፋሉ የሚል ውጥን የነበረው ሲኾን በእቅዱ መሠረት 60 ሺ ነጋዴዎች ማሳተፍ ችያለሁ ማለቱን ከስራ ሐላፊዎቹ ተረድተናል ።


ኩባንያው፣ የንግድ ባለቤቶች 5 ሳጥን(እሽግ ኮካ-ኮላ) ምርቶችን ወይም 3 ሳጥን (እሽግ ፋንታ ኦሬንጅ) ምርቶችን በመግዛት የሽልማት ዕጣ ውስጥ ተሳታፊ በሚኾኑበት ልየታ መሠረት የሽልማት ዕጣ ውስጥ እንዲገቡ አድርግያለኹ ሲል ለመገናኛ ብዙሐን ገልጿል ።


ሲሲቢኤ-ኢትዮጵያ የፍሪጅ ዕጣ ለወጣላቸው ባለዕድለኞች በየንግድ ቤታቸው ድረስ በግንባር ቀርቤ ሽልማቱን አበረክታለሁ ማለቱን አውቀናል ።


ኩባንያው ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተሰጠው ፈቃድ መሰረት ሽልማቱን በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።


የፕሮሞሽኑ የመጀመሪያ ዙር ዕጣ ጥቅምት 14, 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ የወጣ ሲሆን ዕጣ ውስጥ ከገቡ 25 ሺ ተወዳዳሪዎች ዕጣ ለወጣላቸው 70 የመጀመርያ ዙር ተሸላሚ ሽልማት አበርክቶ ነበር።


የንግድ ቤቶች ማክሰኞ ሕዳር 11ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስአበባ ሂልተን ሆቴል በተዘጋጀው የሽልማት ስነ-ስርአት ላይ የፍሪጅ ሽልማቱን ማስረከቡ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።


(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)


                    -Advertisement-