የገጠር መሬት አስይዞ ብድር ማግኘት የሚቻልበት አዲስ ሕግ ሊወጣ መኾኑን ከሚኒስትር ዲኤታዋ ሶፍያ ካሳ ሰምተናል

 ቢዝነስ /ዜና


    Photo:  sofia kassa, state minster of agriculture



መንግሥት የገጠር መሬት ባለይዞታዎች በመሬቱ ላይ ያላቸውን የመጠቀም መብት በዋስትና በማስያዝ ከፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዲወስዱ የሚፈቅድ የገጠር መሬት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ሪፖርተር የአማርኛው እትም ፅፏል።  የፋይናንስ ተቋማት ወይንም አበዳሪው የባለይዞታውን መሬት መጠቀም የሚችለው ከ10 ዓመት ላልበለጠ ጊዜ እንደኾነ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተደነገገ ዘገባው ጠቅሷል።

የግብርና ሚኒስትሯ ሶፍያ ካሳ ከዚህ በቀደመ ጊዜ ለንጋት ፕሬስ- እንደነገሯት ከኾነም በብድር አቅርቦት ዙርያ ከተለያዩ ባንኮች ጋር መስርያ ቤታቸው እየተነጋገረ መኾኑን ተናግረው ነበረ። መሬት የሌላቸው ሰዎችም፣ ባለመሬቶችን ዋስ በመጥራት ገንዘብ መበደር እንደሚችሉ በሕጉ ተደንግጓል ተብሏል። ሚኒስትር ዲኤታዋ ሶፍያ እንደነገሩን፣ ለግብርና የሚሰጠው የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና ለግብርናው የተሰጠው ትኩረት እምብዛም በመሆኑና ገበሬዎች በብድር አጦት ሳቢያ እየተፈተኑ በመኾኑ ነው ብለዋል። ረቂቅ ሕጉ ለህዝብ እንደራሴዎች ቀርቦ ውይይት እንተደሚደረግበት ሶፍያ ነግረውን ነበረ። መንግስት ፣ በተለይም አነስተኛ ማይክሮ ፋይናንሶች ሐላፊነቱን ይወጣሉ የሚል እምነት እንዳለው ገልፀውልናል። ሪፓርተር የአማርኛው ቅዳሜ ይዞት በወጣው ዘገባ ደግሞ ረቂቁ ለምክር ቤቱ መቅረቡን አስነብቧል። የአዲሱ ሕግ ዓላማ፣ የመሬት ባለይዞታዎች ከፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ የእርሻ መሣሪያዎችንና የግብርና ግብዓቶችን እንዲያገኙ ማስቻል ነው።


(ለንጋት ፕሬስ )