አርቲስት መስከረም አበራ ኢቭ የተሰኘን የልጆች ዳይፐር አምባሳደር ሆና ተመረጠች

  




መስከረም አበራ የልጆች ዳይፐር አምባሳደር መሆኗ ተሰምቷል 


በተለያዩ የመድረክና የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በመተወን የምትታወቀው አርቲስት መስከረም አበራ ኢቭ (EVE) የልጆች ዳይፐር አምባሳደር ሆና ተመርጣለች።


Guo peiym አዲስ እና በጥራት ያመረተውን ኢቭ (EVE) የተሰኘውን የልጆች ዳይፐር ለማስተዋወቅ ነው ተብሏል።


ኩባንያው አርቲስቷን የመረጠው በቅርብ ጊዜያት በኪነጥበቡ አለም ያተረፈችው መልካም ሰም ምክንያት መሆኑን በስካይላይት  ሆቴል በተደረገው ስምምነት ተገልጿል።


በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው የአርቲስቷ የአምባሳደርነት ስምምነት የሚቆየው ለአንድ አመት መሆኑን ተነግሯል።


  አርቲስት መስከረም አበራ በEVE የልጆች ዳይፐር ለቴሌቪዥን፣ ቢል ቦርድ እና ለሬድዮ ላይ ማስታወቂያዎች ለመስራት የስምምነት ሰነዱ ያስረዳል፡፡ 


Guo peiym በሕጻናትና ለሴቶች የተለያዩ የንጽሕና መጠበቂያ ምርቶችን የሚያመርት ሲሆን በቅርብ ቀን አዲሱን EVE የልጆች ዳይፐር ለገበያ እያቀረበ ነው።


ኩባንያው የሕጻናት ዳይፐሮችና የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ከ15 ዓመት በላይ ልምድ እንዳለውና  በገበያው ሲሳተፍ መቆየቱን ሰምተናል።


ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ