ዜና/ቢዝነስ
እስካሁንም ለምስራቅ አፍሪካ አባል ሀገራት ክፉኛ እየፈተነ መሆኑን ተገልጿል።
ለፕሮራሙ የሚውል መዋእለ ንዋይ በበቂ ሁኔታ መሰብሰብ እንደተቻለም የገንዘብ ሚኒስቴር አውርቷል።
በኢትዮጵያ ከ20 በላይ ፕሮጀክቶች በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ተከናውኗል ሲሉም የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በሃብት በማሰባሰብ ከ20 በላይ ፕሮጀክቶች መከናወናቸውን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል ።
አቶ አህመድ፣ እንደገለፁት 23ኛው የአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ጉባዔ ተካሂዷል። በጉባኤው ባለፉት አምስት ዓመታት በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ አማካኝነት የተሰበሰበው የሃብት መጠን ምን ያህል እንደሆነና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ተገምግሟል።
በግምገማው በመሰረተ ልማት ትሥሥር ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ነው።
ሚኒስትሩ አክለውም፣ በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚከሰት ድርቅን ለመከላከል የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ እየተከናወኑ ይገኛል። ከጤና ሚኒስትር ጋር ድንበር ዘለል በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮግራም ተነድፎ ወደ ስራ ገብቷል ብለዋል።
ከጅቡቲ ጋር የሚገናኘው የኤሌክትሪክና የቴሌኮም መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክት በኢኒሼቲቩ የሚከናወኑ መሆናቸው ጠቅሰው፣ ከአዲስ አበባ-ጅቡቲ ኮሪደር የሆነው ከአዲስ አበባ በርበራ እና ሚኤሶ_ድሬደዋ ፕሮጀክት ይጠቀሳል።
ከተሰበሰበው ሃብትም ኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት ቀዳሚ ተጠቃሚ መሆን ችላለች ሲሉ ተናግረዋል።
በቀጣይ ተጨማሪ የሃብት ማሰባሰብ ስራ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነስቷል። ይህም በቀጣናው ግዙፍ የልማት ስራዎችን ለምስራት ያስችላል። በተለያዩ ሴክተሮች ላይ ያተኮረ የድንበር አካባቢ ልማት ላይ የሚያትርኩር ፕሮግራም ተቀርፆ ወደ ስራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።