ከሃይማኖትና ፖለቲካ ጋር ተዋህዶ የተከናወነ ጥናት ቀረበ

ዜና


          ዶክተር ደስታ ጥናት ሄሊሶ ሲያቀርቡ


 ሶፎስ አፍሪካ ባለፉት 30 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የተከሰቱ ግጭቶች የብሔር ጉዳይ ከሃይማኖትና ፖለቲካ ጋር ተዋህዶ የተከናወነ መሆኑን በጥናት እንደደረሰበት አስታወቀ።


ሶፎስ አፍሪካ ዛሬ በአዲስአበባ ከተማ በዚሁ ዙርያ ጥናትና ምርምር ጉዳዮች ይፋ አድርጓል።


በጉባኤው ላይ  ብሄርተኝነትን ከፖለቲካ እና ሀይማኖት ጋር መዋሃዱ በህብረተሰቡ ሰላም ላይ የሚያስከትለው ተፅእኖዎችን የዳሰሰ ጥናት ይፋ ቀርቧል።

ስፎስ አፍሪካ የተሰኘው ይኸው ተቋም ጥናቱ የተከናወነው በስድስት ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮችን የሸፈነ መሆኑን ዶ/ር ደስታ ሄሊሶ የሶፎስ አፍሪካ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር ለመገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል።


ጥናቱ በኢትዮጵያ የብሄር ተኮር ፌደራሊዝም እውቅና እና የፖለቲካ ውክልና ቢሰጠውም መለያየትን፣ አለመተማመንንና ብጥብጥ እንዲፈጠር መንስኤ መኾኑን ይጠቅሳል።




የብሄር ተኮር ፌደራሊዝም ለተገለሉ ወገኖች የፖለቲካ ውክልና ቢያሳድግም፣ ለመረጋጋት፣ ለሀብት ኢፍትሃዊነት፣ ለብሔር ብሔረሰቦች ግጭት፣ የውስጥ መፈናቀል፣ ብጥብጥ፣ ሞትና ውድመት አስተዋጽኦ አድርጓል ይላል።


ዘር፣ ሃይማኖትና ፖለቲካ መደባለቃቸውን በተመለከተ ከጥናቱ ግኝቶች መካከል ዋና ዋና ነጥቦች ተጠቅሰዋል።


74 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ጎሳ ለፖለቲካዊ ስልጣን ማእከል ነው ብለው ያምናሉ።


65 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት የብሔር-ሃይማኖት ማንነቶች እና ፖለቲካ በቅርበት የተሳሰሩ ናቸው ብለው ያምናሉ።


80 ነጥብ 4 በመቶ የብሄር ፌደራሊዝም የጎሳ ግጭቶችን ጨምሯል ብለው ያስባሉ።


69 በመቶ ያህሉ የብሄር እና የሃይማኖት ውህደት ወደ መለያየት እና ግጭት ያመራል።


73 ነጥብ 3 በመቶ የብሄር ተኮር ፌደራሊዝም በሰላም አብሮ መኖርን ያደናቅፋል ይላሉ።


45 በመቶ የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች በብሄሮች እና በሃይማኖት ቡድኖች መካከል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።


 በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ አንድነትን ለማምጣት ታጋሽ እና ዘርፈ ብዙ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ደስታ ጥናቱን መሰረት አድርገው ተናግረዋል።


አማኑኤል ክንደያ