ኢትዮጵያን በአለም አደባባይ ያስዋወቀው ተዋቂው ሙዚቀኛ ተፈሪ አሰፋ በ53 አመቱ ህይወቱ ማለፏ አልፏል ።
በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ከማገልገሉ በተጨማሪ በነጋሪት ባንድ ውስጥ ሀገርኛ እና አለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን የጃዝ ሙዚቃ በማቅረብ ይታወቃል ።
ተፈሪ በፖላንድ 7 አመታትን በቆየበት ወቅት ሙዚቃን ተምሮ ከዘማ በራሽ፣ ከዛኪስታን እና ቀሌሎችም ምስራቅ አውሮፓ ተዟዙሮ ስራዎቹን አቅርቧል ።
በአሜሪካ ሀገርም ከጓደኞቹ ጋር በመሆን የራሱን ባንድ መስርቶ ነበር ።
በሀገርቤት በተለይ በአፍሪካ ጃዝ መንደር ውስጥ ነጋሪት ባንድ አማካኝነት ድንቅ ብቃቱን ሲያቀርብ ይታወቃል ።
ኢዮኤል መንግስቱ ፕሮዲስ ባደረገው YEMa አልበም ላይ ከድራም በተጨማሪ የማሊ እና የመካከለኛው አፍሪካ ሙዚቃ መሳሪያዎችን በመጫወት ትልቅ አሻራ አኑሯል ።