9ኛው ኢትዮ ኸልዝ የጤና አውደርእይ በአዲስአበባ ሊካሄድ መሆኑን ተገለፀ

 ዜና/ቢዝነስ 


ከ4000 በላይ የጤና ባለሞያዎችና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት አውደ ርእይ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር በመተባበር 4ኛ ዓለማቀፍ የአቅራቢዎች ጉባኤም ይከናወናል መባሉን ሰምተናል።


በዚሁ ዝግጅት ላይ ከአስር አገራት የተውጣጡ ከዘጠና በላይ  ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ይሳተፉበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በህክምናው ዘርፍ የመድኃኒት አቅርቦት የእሴት ሰንሰለት ትኩረት ያደረገ ኤግዚቢሽን መሆኑን ተገልጿል።

በዚህ ጉባኤ ላይ በሕክምና ዘርፍ ያሉ እውቀቶችን ማስተላለፍ እና የጤና ባለሞያው የብቃት ማረጋገጫ እውቅና የሚሰጥበትና የሚታደስበት ሁኔታዎችንም መዘጋጀቱንም የአውደርእና ኤግዚቢሽን አዘጋጆች ገልፀዋል።

በአውደ ርእዩ የጤና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት መሆኑን የተገለፀ ሲሆን 
በኢትዮጰያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሚዘጋጀው 4ኛው ዓለም ዓቀፍ የአቅራቢዎች ጉባዔም ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢትዮ ኸልዝ ጎን ለጎን ይከናወናል ተብሏል።

አውድ ርዕዮ ከ18 አመት በላይ ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት የሚታውቀወ ፕራና ኤቨንትስ አስተባባሪነት የሚቀርብ ሲሆን በጤና እንክብካቤ፣ በህክምና መገልገያዎችና መድሃኒት የእሴት ሰንሰለት ለማስተሳሰር የተዘጋጀ መሆኑን በመግለጫው ላይ ሲገለፅ ሰምተናል ።

ኢትዮ ኸልዝ ዓለም ዓቀፍ ዓውደ ርይና ጉባኤ ለ9ኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።

በመክፈቻ ስነስርአቱ  ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት እንደሚከፈት አዘጋጆቹ ፕራና ኤቨንትስ ተናግሯል ።

በኤግዚቢሽኑ ከ10 ሀገራት የተውጣጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበትና አዳዲስ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎችን በማስተዋወቅና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮ ኸልዝ በጤና ዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ማህበረሰብ አካላት እና የጤና ባለሙያዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት ማሳደግና በመድሃኒት አቅርቦት ዙሪያ ለተጋረጡ ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች የመፍትሄ ይሰጣል የሚል ውጥን ተይዞለታል።

ከ4000 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ የዘርፉ ንግድ ማህበረሰብ አካላት ምርት እና አገልግሎታቸውን ማስተዋወቅ የሚችሉበትን በኢትዮጵያ ብቸኛው የጤናው ዘርፍ መሰባሰቢያ መድረክም ነው ተብሏል።

 የህክምና አገልግሎት ፍላጎት ለማሳካት የሚያስችሉ ቴከኖሎጂ የሚያቀርቡ ከቻይና፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ አሜሪካ፣ ኬንያ፣ ፖርቹጋል፣ ቱርክ ፣ ኦስትሪያ እና የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ መሰረታቸውን ያደረጉ ኩባንያዎች ከአውደርዕዩ ይሳተፋሉ። 



 በአማኑኤል ክንደያ
    [አርታኢ]