የሆሊውድን የፊልም አስተሳሰብ ላይ አሻራ ያሳረፈው ኃይሌ ገሪማ

 



ፕሮፌሰር  ኃይሌ ገሪማ የፊልም ደራሲ ነው።በርካታ ፊልሞችን ፅፏል፣ መርቷል። በሆሊውድ መንደር ከፍተኛ አድናቆትና ስም ያለው ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪ ነው።


ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የካቲት 25 ቀን 1938 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ከደራሲ አባታቸው ገሪማ ታፈረና ከመምህርት እናታቸው ተወለደ፡፡ 


በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገው ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ አባቱ ገሪማ ታፈረ የትያትር ቡድን ውስጥ በመስራት ነበር፤ ወደ ኪነ ጥበቡ የገባው፡፡ 


ገሪማ ታፈረ የተዋጣለት ከያኒ ከመሆኑም በላይ 

ብዙውን ጊዜም ታሪካዊ እና እውነተኛ የኢትዮጵያን ባህል የሚያንፀባርቁ ወጥ ድራማዎችን ይሰሩ ነበር፡፡


በኪነት ቤተሰብ ውስጥ የተገኘው ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ  በ21 ዓመቱ ነበር ወደ ውጭ አገር ለትምህርት የሄደው፡፡


እ.ኤ.አ በ1967 ወደ ቺካጎ ጉድማን የድራማ ት/ቤት ለመማር ከሄዱ በኋላ ሲኒማ ከትያትር የበለጠ ማሳየት የፈለገውን ሁሉ ማሳየት ስለሚያስችለኝ በማለት ወደ ፊልሙ አዘነበለ ፡፡ 


በዚህምመሰረት ከካሊፎርኒያ ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን “Bachelor’s and Master’s of Fine Arts degrees in film” አግኝተዋል፡፡




 ፕሮፌሰር ኃይሌ ከአስተማሪነቱ ጎን ለጎን የሚሰሯቸው የፊልም ስራዎች በይዘት እና አቀራረባቸው ከሌሎች ፊልሞች የተለየ ከፍታ ያላቸው ናቸው።


“ጤዛ” የተሰኘውን ፊልም በአማርኛ በመስራት ብቃቱን ያሳየና  በኢትዮጵያውያን የፊልም ታዳሚዎች ዘንድ አስመስክሯል ፕሮፌሰር ኃይሌ።


ፕሮፌሰር ኃይሌ በአለም ዓቀፍ ደረጃም እውቅና ያገኙባቸውን በርካታ ፊልሞች ሰርቷል፡፡


በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ በኢትዮጵያ የነበረውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታ ማራኪ በሆነ አቀራረብ ባሳዩበት "ጤዛ ፊልም" በጎንደርና በአዲስ አበባ ከተሞች እንዲሁም በጀርመን ሀገር የኢትዮጵያውያንን አኗኗር ፍንትው አድርጎ ያሳየበት ነው ማለት ይቻላል።

 

ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ  “ጤዛ ፊልም” በአማርኛ ፊልሞች ላይ ተሞክረው የማያውቁ የፊልም አሰራር ቴክኒኮችን በመጠቀም እና ፊልም እንኳን በተውኔት ለመሳተፍ ይቅርና ተመልክተው  የማያውቁ ተዋናዮችን በማሳተፍ አስደናቂ የፊልም ዳይሬክቲንግ ብቃቱን ያሳየበት ነው።


በጎርሳውያኑ አቆጣጠር ከ1975 ጀምሮ በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ የፊልም አሰራር ጥበብ መምህር ሲሆኑ በጎርሳውያኑ 1993 በሰራው "ሳንኮፋ ፊልም"  የተሰኘውን ከፍተኛ አለምአቀፍ እውቅና እና ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡


ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ከሰሯቸው ፊልሞች ሰባት ያህሉ በተለያዩ የአለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሸላሚ ነው፡፡ 


ፊልሞቻቸው በአፍሪካውያን እና በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። የራሳቸውን እንዲሁም ስለ አፍሪካውያን እና በአፍሪካውያን የተሰሩ ፊልሞችን የሚያሰራጩበት "ማይ ፈዱ" የተባለ ፊልም ማሰራጫ ድርጅትም መስርቷል፡፡


ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ከሰሯቸው ፊልሞች መካከልም በጥቂቱ እነኚህ ናቸው።


1972 – Hour Glass Hour Glass

1972 – Child of Resistance

1976 – Bush Mama

1976 – Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)

1978 – Wilmington 10 — U.S.A. 10,000

1982 – Ashes and Embers

1985 – After Winter: Sterling Brown

1993 – Sankofa

1994 – Imperfect Journey

1999 – Adwa – An African Victory

2009 – Teza




ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ሽልማቶችን  ተቀብሏል። ከበሬታ ያለው ባለሞያም ጭምር ነው።