- ኢትዮጵያ ከወርቅ ሽያጭ የምታገኘውን ገቢ ማሽቆልቆሉ ተነገረ።
የዘንድሮው ጠቅላላ የውጭ ንግድ ገቢ በ12 በመቶ ወይም በ500 ሚሊ ዶላር መቀነሱን የማእድን ሚኒስቴር ተናግሯል ።
ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ዓመት ከወርቅ ሽያጭ ያገኘችው ገቢ ከባለፈው ዓመት በ333 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ቀንሷል ተብሏል።
በበጀት ዓመቱ ከማዕድን ዘርፍ የውጭ ንግድ የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ከባለፈው በጀት ዓመት ገቢ ጋር ሲነጻጸር በ323 ሚሊዮን ዶላር መቀነሱም ተገልጿል።
ከአንድ ወር በፊት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፍ የውጭ ንግድ 251 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱና ይህም ከአጠቃላይ የውጭ ንግድ ገቢ 6 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚሸፍን ተገልጿል።
(ንጋት ፕሬስ)

