Azizze usman, social media infulencer
Photo by ; Moges mokonenn
አዚዝ ዑስማን የቱሪዝም አዲስ እሳቤ ሊያስተዋውቅ ወጥኗል።
ከዱባይ ንጉስ እጅ ተሸላሚ ወጣት አዚዝ ዑስማን (appousto )
ኢትዮጵያን ለመላው ዓለም የሚያስተዋውቀው ካሪቡ ግሩፕ መሥርቷል።
መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ የኢትዮጵያን ቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለመላው ዓለም ማስተዋወቅን ዓላማው ያደረገ፣ ካሪቡ ግሩፕ የተሰኘ ዓለማቀፍ ኩባንያ ነው፡፡
የካሪቡ ግሩፕ መሥራች ኢትዮጵያዊው አዚዝ ኡስማን፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ቦሌ በሚገኘው ማዶ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ ከዱባይ ኢትዮጵያ ስለመጣበት ዓላማ፣ ካሪቡ ግሩፕ ስለሚሰራቸው ሥራዎችና ስለወደፊት ዕቅድና ራዕዩ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ካሪቡ ግሩፕ በዋናነት ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ የተመሰረተ የግል ቢዝነስ ተቋም ነው የተባለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ምርቶች በዓለማቀፍ ገበያ ውስጥ ስመጥር እንዲሆኑና የኢትዮጵያን ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ እንዲሁም የአገሪቱ ባለሃብቶች በዓለማቀፍ ደረጃ መድረክ የሚያገኙበትና ተወዳዳሪነታቸው የሚጨምርበትን ዕድልለማስፋት የሚተጋ ኩባንያ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
በሳኡዲ አረቢያ ተወልዶ በዱባይ ትምህርቱን የተከታተለው ወጣቱ ኢትዮጵያዊ አዚዝ ኡስማን፣ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም በኢኮኖሚክስ የማዕረግ ሽልማትን ከዱባይ ንጉስ ሼክ መሃመድ ቢን ረሺድ እጅ የተቀበለ ብቸኛው አፍሪካዊ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን የአገሪቱ ወጣቶች ሚኒስትር ክብርና ዕውቅና ከሰጧቸው ጥቂት ስኬታማ ወጣቶች አንዱ ነው ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 ዓ.ም ዓለማቀፉ የነዳጅ አቅራቢ ቶታል የመካከለኛው ምሥራቅ የክብር አምባሳደር አድርጎ የሾመው አዚዝ፤ የግዙፉ ዓለማቀፍ የንግድና መዝናኛ ማዕከል የሆነችው ዱባይ የክብር አምባሳደር በመሆንም መሾሙ ተጠቁሟል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተገኙበት በተካሄደው በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ማህበራዊ ሚዲያውን አገርን ለማስተዋወቅ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል እንዲሁም አገርን የሚያስተዋውቅ ብራንዲንግ እንዴት መሥራት እንደሚቻል ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ በቅርቡም በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተነግሯል፡፡
ራሴን እንደ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሳይሆን እንደ ቢዝነስ ሰው ነው የማየው የሚለው አዚዝ ኡስማን፤ በማህበራዊ ሚዲያ የኢንስታግራም ገጹ ከ1ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን ማፍራት እንደቻለ ታውቋል፡፡
ወጣት አዚዝ ኡስማን በአሁኑ ወቅት ደግሞ፣ ያካበተውን እውቀት፣ ልምድና ዝናውን በመጠቀም ተቀማጭነቱን ዱባይ ውስጥ ያደረገ እና የአገሩን ኢትዮጵያን ቱሪዝም ለማሳደግ እና የውጭ ኢንቨስተሮችን ወደ አገሪቱ ለመሳብ የሚሰራ ካሪቡ ግሩፕ የሚባል ድርጅት አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ከካሪቡ ግሩፕ አላማዎች መካከል ኢትዮጵያዊ የሆኑ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ስመጥር እንዲሆኑ ማስቻል፤ የኢትዮጵያን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ማሳደግ እንዲሁም የአገሪቱን ባለሃብቶች በዓለም ዓቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ለማድረግ በግል ከሚደረጉ ጥረቶች ባለፈ በተቋም ደረጃ ስራዎችን መስራት
እንደሚሰራ የካሪቡ ግሩፕ መስራች ወጣት አዚዝ ኡስማን ተገልጿል።
ኤግል ኤቨንት ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባሰናዳው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።