የኢትዮጵያ መንግሥት በዘንድሮው በጀት ዓመት የ500 ሺሕ ሴቶችን የጉዞ ወጪ ችሎ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ ሥልጠና በመስጠት ላይ ሲሆን፣ የመጀምሪያ ተጓዦች አምና መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ መጓዛቸው ይታወቃል ፡፡
ይሁን እንጂ በሳውዲ አረቢያ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በዘፈቀደ መታሰራቸውንና አሰቃቂ በሚባል ደረጃ ሰብአዊ መብቶቻቸውን እንደሚጣስ በሳኡድ አረብያ ሳኡዲ ኑሯቸውን ከሚኖሩ ምንጮቻችን አረጋግጠናል።
ሌሎችንም ሳኡዲ በከፍተኛ እንግልት ከአገሯ እንዲወጡ ማድረጓ ምንጮቻችን ነግረውናል።
በፈርንጆች 2020 የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት በሳውዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስቃይና መገደል ካረጋገጠ በኋላ የአገሪቱን የሰብዓዊ መብት አያያዝ የሚያወግዝ ውሳኔ አሳልፎ ነበር፡፡
ሠልጣኞች ከመንግሥት በኩል" እድሉ ሊያመልጣቸው የማይገባ የሕይወት ዘመን ወርቃማ እድል ነው " እየተባሉ የውሸት እንደሚደለሉ እንዳለ ተረድተናል ፡፡
ለቤት ሠራተኝነት የሚሄዱት የኢትዮጵያ ሴቶች በወር 260 ዶላር ግድም እንደሚከፈላቸው ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የወጣ አንድ ሰነድ ተመልክተናል ። ከ18 እስከ 40 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ የኮሌጅና የዩንቨርሲቲ ምሩቃንንም ያካተተ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞችን ለተሳዳቢ አሠሪዎች አሳልፎ የሚሰጠውን "የካፋላ ስርዓትን ማፍረስን ጨምሮ ሙሉ ጥበቃን ለማረጋገጥ መፍትሔ መፈለግ እንዳለበት የስደተኞች መብት ተመራማሪ ናድያ ሃርድማን ለአልጀዚራ ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበረ።
የሚሰነዘረው ወቀሳ በተመለከተ ከኢትዮጵያ የሚላኩት ሴት ሠራተኞች ከሳውዲ አረቢያ የሠራተኛ ጥበቃ ሕጎች የተገለሉ ናቸው የሚል ነው። ለሚደርስባቸው በደልም ምንም ዓይነት ሕጋዊ መፍትሔ የሌላቸው መሆኑ የሰብኣዊ መብት ተቆርቋሪዎች ይናገራሉ ፡፡
በሳኡዲ ያለው ካፋላ በተሰኘው ስርዓት አንድ ሠራተኛ በደል ቢደርስባት እና ከአሠሪዎቿ ብትሸሽ ፓስፖርቷን ጨምሮ የተለያዩ የሰነድ መረጃዎቿን እንድታጣ እንደሚደረግ እና ይህ ስርዓት አሁንም ለውጥ እንዳልተደረገበት ነው እየተናገረ ይገኛል ፡፡
አሁንም ቢሆን በርካታ ስደተኛ ሠራተኞች በሳውዲ አረቢያ ከሠራተኛ ሕጎች የተገለሉ በመኾናቸው በዘመናዊ ባርነት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡
(ንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)

