የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ቢሮ ድጋፍ ለሚያሰፈልጋቸው ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቅያ የሚውል የ4.2 ሚልየን ብር የዐይነት ድጋፍ ተረከበ


      photo : የቢሮው ሓላፊ ወይንሸት ዘሪሁን



 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት ጋር በመነጋገር ከ4.2 ሚልየን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ከጎዳና ኑሮ ለተነሱ ሴቶች ማበርከቱ ተሰማ።


የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአት ልማት ድርጅት በከተማዋ ለሚገኙ ከጎዳና ለተነሱ ወጣት ሴቶች የሚውል ድጋፍ ዛሬ ለቢሮው አስረክቧል ።


ድጋፍ ያገኙት በቢሮው ስር የሚተዳደሩ ለቀጨኔ ታዳጊ ሴት ህፃናት ማቆያና ማቋቋሚያ ማዕከል ፣ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ሴቶች፣ በመዲናዋ ለሚገኙ የተመረጡ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሴት ተማሪዎች እንዲሁም እቴጌ መነን 2ኛደረጃ የሴት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት የሚውል መኾኑን  ተነግሯል ።




ከ77,000 በላይ ሞዴሶች የተበረከተላቸው ሲሆን አጠቃላይ የ4.2 ሚልየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ናቸው ተብሏል ።


በርክክብ ስነ- ስርአቱ የአዲስአበባ ከተማ የሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ቢሮ ሐላፊ ወይንሸት ዘሪሁን እንዲህ ያለውን መልካም ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር መኾኑን ጠቁመው፣ በተለይም የግል ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

 

የቢሮ ሓላፊዋ ወይንሸት ዘሪሁን ማህበራዊ ሐላፊነታቸው የሚወጡ መንግሥታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የኩባንያዎች ሊበረታቱ ይገባል ማለታቸውን ሰምተናል።


      Photo:የቢሮው ኮሙኒኬሽን ሐድጉ ፀሐየ

    

የአዲስአበባ ሴቶች ፣ህፃናትና ማህበራዊ ቢሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ እንደሚያደርግ ሐላፊዋ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ተናግረዋል ።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት፣ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ - ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብትና ደህንነታቸው እንዲከበር ብርቱ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል ።

 የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ  ተጠቃሚነታቸውና ውክልናቸው እንዲረጋገጥ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ  መሆኑን ከሐላፊዋ ወይንሸት ዘሪሁን ተረድተናል ።




(ንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)