ቢዝነስ/ዜና
የፕራና ኤቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ
የእንስሳት ዘርፍ አውድ-ርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ።
አውደ-ርዕዩና ጉባኤው ከጥቅምት 15- 17 በሚሊንየም አደራሽ ተከፍቶ ለጎብኝዎችና የእንስሳት ዘርፍ ስራ አከናዋኞች ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል ።
አውደ-ርዕዩ ከግብርና ሚኒስቴር ፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፣ ፓን አፍሪካ ንግድ ምክርቤት ፣ የኔዘርላንድ ኤምባሲና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል ።
12ኛው ኢትዮ ፓሊተሪ ኤክስፓ፣ 8ኛው የአፍሪካ እንስሳት አውደርዕይ እና 3ኛውአፒካልቸር እና አኳ ካልቸር ኢትዮጵያ የንግድ ትርኢት ያላቸው ዋነኛ የንግድ ስራ አቀለጣጣፊዎች የሚሳተፉበት መኾኑን የአውደ-ርዕዩ አዘጋጅ ፕራና ኤቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ ሲናገሩ ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሳትፎ ጨምሮ ከ17 አገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት አውደ ርዕይና መኾኑን ተመልክተናል ።
50 በመቶ የተሳታፊ ኩባንያዎች እና የማሳያ ቦታ ሽፋን ዕድገት ባሳየው በዚህ አውድርዕይ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ስመጥር የሀገር በቀል ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተነግሯል ።
ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት ዓውደ-ርዕይ እና ጉባዔዎች ለዶሮ፣ ወተት፣ እና ስጋ ንዑስ ዘርፎች ዕድገትና ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱ በመክፈቻ ንግግር ተገልጧል ።
እነዚህ ኹነቶች የዘርፉ ባለሙያዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ ትልቁ መሰባሰቢያ በመሆናቸው የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ የእውቀት ሽግግርን በማምጣትን ጨምሮ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማረጋገጥ መቻላቸውን የፕራና ኢቨንትስ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ለማ ተናግረዋል፡፡
በዚህ አውደ-ርዕይ ዓቀፍ የእንስሳት ሀብት እሴት ሰንሰለት፣ የኢትዮ ዶሮ ኤክስፖ፣ የአፍሪካ የእንስሳት ሀብት ፣ የኢትዮጵያ የአሳ ኤክስፖና የኢትዮጵያ የማር ምርቶች ተካተውበታል ተብሏል።
አጠቃላይ የእሴት ሰንሰለቱን የሚወክሉ በካናዳ፣ ቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ጀርመን፣ ሃንጋሪ፣ ህንድ፣ ኬኒያ ጆርዳን፣ሊባኖስ፣ ኔዘርላንድሰ፣ ስኮትላንድ፣ ስፔን ፣ ቱርክ፣ ዩክሬይን፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ መሰረታቸውን ያደረጉ ዓለም ዓቀፍ የዘርፉ ተዋናዮች የሚሳተፉበት ነው።
እነኝህ መሰረታቸው ውጭ አገራት ያደረጉ የንግድ አቀለጣጣፊዎች ሀገር በቀል ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት የሚያደርጉበት መኾኑንም ተረድተናል።
በአውደ-ርእዩ የፕራና ኤቨንትስ መስራችና ማነጂንግ ዳይሬክተር ነብዩ ለማ፣ የፓን አፍሪካ ንግድ ምክርቤት ፕሬዚዳንት ክቡር ገና ፣ የኔዘርላንድ ኤምባሲ አምባሳደር ሔንክ ጃን ቤከር ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሞያዊ ንግግር በማድረግ መከፈቱን መታዘብ ችለናል ።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



