ቢዝነስ/ዜና
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ (ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ሰብሲደሪ ድርጅት) የመጀመሪያው ዙር 70 የፍሪጅ ዕጣ በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ማከናወኑ ተነገረ።
ኩባንያው የንግድ ቤቶቹን ለማበረታታት ለባለዕድለኞች የፍሪጅ የሽልማት እጣ ማበርከቱን ከቦታው ተገኝተን ተመልክተናል።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ (ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ሰብሲደሪ ድርጅት) "ይግዙ ፣ ይሽጡ ፣ ይሸለሙ" በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ቀጥተኛ የንግድ ደንበኞቹን ለማበረታታትና የንግድ ስራቸው ለማቀለጣጠፍ ይረዳቸው ዘንድ የፍሪጅ ሸልማቶችን ማበርከቱን ተረድተናል።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተሰጠው ፈቃድ መሰረት የሽልማት መርኃ ግብሩን በአስተዳደሩ ቅፅር ጊቢ በሚገኘው አደራሽ ማከናወኑን ተመልክተናል ።
በአጠቃላይ 75,000 የንግድ ተቋማት የሚሳተፉበት ሲኾን አሁን ላይ 25,000 ቀጥተኛ የንግድ ተቋማት የዕጣ ሽልማቶች የተሳተፉበት የሽልማት ዕጣ ተካሄዷል። የዕጣ አወጣጥ ሰነስርአት ከ25,000 ተሳታፊዎች 70 እድለኛ የንግድ ድርጅቶች የፍሪጅ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በቀጣይ ከአንድ ወር በኃላ ለ25,000 ቀጥተኛ የንግድ ተቋማት በእጣ አወጣጥ ሰነ ሰርአት የሚሳተፉበት ሰነ ስርአት መርኃ ግብር መዘጋጀቱን የኮካኮላ ኩባንያ ማርኬቲንግ ማናጀር አብነት ፀጋዬ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ከነዚህ መካከልም እድለኛ የንግድ ተቋማት ፍሪጆች እንደሚበረከትላቸው ተነግሯል።
የማርኬቲንግ ማናጀር አብነት ፣ ኩባንያው ሌላኛው የሽልማት መርኃ ግብር ከአንድ ወር በኃላ ለማከናወን በዝግጅት ላይ እንዳለ ተናግረዋል ።
የዕጣ ውድድሩ ነሃሴ 29 የጀመረ መኾኑን ኩባንያው እወቁልኝ ብሏል።
በሁለቱም ዙር የዕጣ አወጣጥ ሰነሰርአት 50,000 የንግድ ባለቤቶች በዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ተሳትፈዋል ሲል ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ (ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ሰብሲደሪ ድርጅት ) አስታውቋል ።
የሽልማት መርኃ ግብሩ የኩባንያው ደንበኞች በተቋሙ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እንደ ቴሌግራም ፣ የፌስቡክና የኢንስታግራም ባሉ መገናኛ ዘዴዎች መመልከት ትችላላችሁ ተብላቹኃል።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አ.ማ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ደንበኞቹን የንግድ ስራቸው እንዲሳለጥላቸው እና እግረ መንገዱን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት መኾኑን በመረሀ ግብሩ ወቅት ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ተናግሯል።
ኮካኮላ ኩባንያ ከዚህ ቀደም የሽልማት እጣ የሚያከናውነው ለደንበኛች ሲያከናውን መቆየቱን ንጋት ፕሬስ ከስራ ኃላፊዎቹ ሰምታለች።
አኹን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የንግድ ተቋማት ያለባቸውን የተለያዩ ችግሮች በመመልከት የፍሪጅ የሽልማት እጣ እንደጀመረ ተገልጿል።
የዚህ ሽልማት እጣ አላማውም የንግድ ተቋማት ያለባቸውን ችግር ለማቃለልና ለማገዝ ሁነኛ መላ ሁኖ መገኘቱን ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ ሰብሲደሪ ድርጅት ማርኬቲንግ ማናጀር አብነት ፀጋዬ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ተናግረዋል።
(ለንጋት ፕሬስ አማኑኤል ክንደያ)



